እልባት አጣ የተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኤርትራ | አፍሪቃ | DW | 03.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

እልባት አጣ የተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኤርትራ

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ሪፖርት አቅራቢ ፤ በኤርትራ ሳይቋረጥ የቀጠለው የሰብአዊ መብት ጥሰት በተለይም በብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት ረገድ የሚታየው እጅግ የሚያሳስብ ነው ሲሉ ድርጅቱ ሁኔታውን እንዲከታተሉ ያሠማራቸው ወ/ት ሼይላ

ቢ , ኬታሩት ገለጡ። ኬታሩት ጀኔቭ ላይ ይህን መግለጫ የሰጡት፤ በጀርመንና በእስዊትስዘርላንድ ከመጋቢት 8 እስከ 19, 2006 ጉብኝት አድርገው እንደተመለሱ ነው። ኬታሩት ፣ በውጭ ከሚኖሩ ኤርትራውያን ስደተኞች በቀጥታ ያዳመጡት ብሶት ከዚህ ቀደም በዚያች ሀገር ስለሰብአዊ መብት አያያዝ የቀረቡ ዘገባዎችን ያጠናከረው መሆኑን ነው ያስረዱት። አሁን ሞሪሸስ የሚገኙትን የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት አቅራቢ ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ሼይላ ኬታሩት ፤ ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት አገር ተገኝተው ያዩትን ፤ የሰሙትን ፣ ማቅረብ አልቻሉም ። በዚያ ተገኝተው ይህን ለማድረግ ያልቻሉትም የኤርትራ መንግሥት ቪዛ ስላልሰጣቸው መሆኑን ጠቁመዋል። ኤርትራውያን በብዛት አገር እየለቀቁ የሚሰደዱበት ዋና ምክንያት ኬታሩት እንዳሉት ብሔራዊ ወታደራዊ አገልግሎት ነው። የኤርትራውን ብሔራዊ ወታደራዊ አገልግሎት ከሌሎች ሃገራት አሠራር ምን የተለየ እንደሚያደርገው ተጠይቀው ሲመልሱ--

«ከቀድሞ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ምልምሎችና ከዚህ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ካመለጡ ወገኖች እንደሰማኹት አገልግሎቱ መቋጫ የሌለው፣ አስገዳጅ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከዞህ ጋር ተያይዞ ሰብአዊ መብትን በጣሰ መልኩi ከባድ ቅጣት የሚሰጥበት መሆኑ ነው። አገልግሎቱ 18 ወራት ነው ቢባልም፤ --6 ወር ወታራዊ ሥልጠናና የ 12 ወራት የአገልግሎት መርኀ ግብር ቢኖርም፤ --ማለት በውትድርናው ዘርፍ ወይም በተለያዩ ሚንስትሮች ሥር የሲቭል አገልግሎት መስጠት ሲሆን፤ ይህም እንደነገሩኝ ፣ ከ 18 እስከ 50 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ወንዶችንና ሴቶችን ይመለከታል። አገልግሎቱ፣ መቋጫ የሌለው ፤ ጨርሶ መሰናበት የማይቻልበት ሁኔታ ነው።»

ኬታሩት ፤ ስለብሔራዊ የውትድርና አገልግሎቱ አያያዝ የሚያማርሩት ወገኖች ነገሩኝ እንዳሉት ከሆነ የደመወዙ መጠን፤ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም፤ የቤተሰብ አባላትን ለመደገፍ የማያስችል ነው። ሃይማኖታቸው በውትድርና መሳተፍን የማይፈቅድላቸውም ቢሆኑ ይገደዳሉ እንጂ አማራጭ አገልግሎት የመስጠት ዕድል የላቸውም።በትምህርታቸው በርትተው የሚገኙ ወደ ዩንቨርስቲ የመግባት ዕድል አላቸው ፣ ወደ ውጭም ለከፍተኛ ትምህርት ሊላኩ ይችላሉ ስለመባሉ የተከታተሉት ጉዳይ እንዳለም ጠይቀናቸው ነበር።

«እኔ እንደምገነዘበው ከሆነ ይህ ብዙ ፉክክር የሚታይበት ሁኔታ ነው። ማንኛውም ተማሪ ወደ ዩንቨርስቲ መግባት አይችልም። እንደተገነዘብኩት የአሥመራ ዩንቨርስቲ ተዘግቷል። ኮሌጆች ክፍት ናቸው ነገር ግን በውጤት ረገድ ውድድር አለ። ያን ያህkle በቀላሉ የሚገቡበት አይደለም። የከፍተኛ ደረጃ ትምህርትን ከትትል በተመለከተ የምለው ይህን ነው። ወደ ውጭ ሄዶ የመማር ዕድል ስላላቸው ተማሪዎች ፣ እስካሁን ከአነዚህ ዓይነቶቹ ተማሪዎች ጋር የመነጋገር ዕድል አላጋጠመኝም።ስለዚህ በበዚህ ነጥብ ላይ ለመናገር ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብኛል።»

የተባበሩት መንግሥታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የኤርትራ ጉዳይ ዘገባ አቅራቢ ወ/ት ሼይላ ኬታሩት፤ በናጋድ ፤ ጂቡቲ እንደታሠሩ የሚገኙ የ 276 ኤርትራውያን ይዞታና 2 በእሥር ላይ መሞታቸው እንዳሳሰባቸው ከመግለጻቸውም ዓለም አቀፊ ማሕበረሰብ፤ ለሚሰደዱ ኤርትራውያን ጥበቃ በማድረግ ቢያንስ፤ በዓለም አቀፍ የስደተኞች አያያዝ ደንብና የሰmbeአዊ መብት ጥበቃ ደንብ ጊዜያዊ መጠለያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።የኤትራ መንግሥት ዓለም አቀፍ ግዴታዎችን መፈጸም እንደሚኖርበት ሲያስታውሱ፤ አንዱ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ስላሉት ነጥብ እንዲህ ነበረ ያሉት--

«ኤርትራ በሰብአዊ መብት አያያዝ ረገድ እንድታከናውናቸው እ ጎ አ በ 2009 የቀረቡት የሰብአዊ መብት ነክ ጉዳዮች በ 2014 ም በድጋሚ መቅረብ ያለበት ይመስለኛል።አንዱ የማስበው፤ በግፍ ቁም ስቅል ማሳያ ርምጃ፤ እንዲወገድ ሕግ ይጸድቅ ዘንድ የሚጠይቀውን ደንብ ነው።»

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ ቅርንጫፎች ILO , UNESCO ና የመሳሰሉት በሚያተኩሩባቸው ጉዳዮች ረገድ ግፊት ማድረግ እንደሚችሉ፤ አካባቢያዊ ድርጅቶች፣ ለምሳሌ ያህል የአፍሪቃ ሕብረት ፤ የአፍሪቃ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፣ ደንብ በፈቀደ መጠን በጉዳዮች የሚገቡበትና የሚበጅ ተግባር መፈጸም እንደማይሳናቸው የጠቆሙት ኬታሩት፤ ስለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ድርሻ ተከታዩን ብለዋል።

«ዓለምአቀፉን ማህበረሰብ በተመለከተ ፣ የእኔ እምነት ነው፣ ሰብአዊ መብት ዋና መወያያ ርእስ ሊሆን ይገባልየተለያዩ አገሮች ከኤርትራ ጋር በሚደረግ ስብሰባ ለዚህ ትኩረት እንዲሰጡ፤ ሀገራት የጋራና ሌሎችንም የግንኑነት ደንቦች በማጤን፤ በኤርትራና በሌሎች 3ኛ አገሮች ንግግር ፤ ችግሮች እንዲቃለሉና ኤርትራውያን ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ማብቃት ነው።ኤርትራውያን አገር ለቀው የሚሰደዱባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፤ የመሳደድ ሥጋት፤

ኢሰብአዊ ድርጊት፤ በግፍ ርምጃ ቁምስቅል ማሳየት፤ ለውትድርና አስገድዶ መመልመልና ማለቂያ በሌለው ብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት ማሠማራት ናቸው። እዚህ ላይ የምናገረው ስለስደተኞችና በዚህ ተገን ጠያቂዎች ስለሆኑት ነው።በመጨረሻም፤ ሲቭሉ ማሕበረሰብ በማንኛውም መድረክ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን በማንሳት ጠቃሚ ሚና እንዳለው አምናለሁ። »

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic