ኤፍሬም ሃጎስ እና የበጎ ፍቃድ ስራው | ባህል | DW | 14.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ኤፍሬም ሃጎስ እና የበጎ ፍቃድ ስራው

የዛሬው የወጣቶች እንግዳ አዳጊ ወጣቶችን እያበረታታ ፤ አንድ ቀን የብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ሆነው ለአገራቸው እንዲሳተፉ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። ስለዚህ የበጎ ፍቃደኝነት ስራው ያጫውተናል።

ከነገ በስተያ(እሁድ) ለአለም እግር ኳስ ዋንጫ የአፍሪቃን ማጣሪያ ለማለፍ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪቃ ብሔራዊ ቡድን ጋ አዲስ አበባ ውስጥ የመጨረሻ ግጥሚያውን ያደርጋል። የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ጨዋታ አፍቃሪዎች የሌሎች አገሮችን ግጥሚያዎች ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም የአፍሪቃ ዋንጫ በመሳሰሉ ግጥሚያዎች የሚያደርገውን ተሳትፎ እየተመለከትነው ነው።ይሁንና በአለም ታዋቂ የሆኑ ተጫዋቾችን ለማፍራት ብዙ መሰራት ይኖርበታል። የዛሬው የወጣቶች እንግዳ አዳጊ ወጣቶችን እያበረታታ ፤ አንድ ቀን የብሔራዊ ቡድን እግር ኳስ ተጫዋቾች ሆነው ለአገራቸው እንዲሳተፉ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ኤፍሬም ሃጎስ ይባላል። ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው። የልጅነት ህልሙ እግር ኳስ ተጫዋች መሆን ነበር። ነገር ግን ኤፍሬም በህይወቱ ብዙ ፈተናዎች ገጥመውት ስለነበረ ምኞቱን ዕውን ማድረግ አልቻለም። ይሁንና ሌሎች አዳጊ ወጣቶች ይህንን እድል እንዲያገኙ የበኩሉን በማድረግ ላይ እንደሆነ ገልፆልናል።

ኤፍሬም በስምንት ዓመት ልጅ ሳለ ነው አባቱ የሞቱት። የሳቸውም መሞት ለዕሱ ፣ለታላቅ ወንድምና እህቱ ህይወትን ይበልጥ አከበደባቸው። ያኔም ኤፍሬም በልጅነቱ የጎዳና ህይወትን መተዋወቅ ነበረበት። ገንዘብም ለማግኛ ታላቅ ወንዱሙም ጫማ እንዴት እንደሚጠረግ አስተምሮት ከኑሮ ጋ ትግል ጀመረ።

ዛሬ ኤፍሬም 28 ዓመቱ ነው። በአገር አስጎብኚ እና በትርጉም ስራ በግሉ ይተዳደራል። ከዛ በፊትም ረዳት መምህር እና የእንግዳ መቀበያ ቤት ስራ አስኪያጅ በመሆን አገልግሏል። ይህም በጊዜ ህይወቱን ማቃናት በመቻሉ እንደሆነ ይናገራል። እሱም በበኩሉ አንድ ጥሩ አስተዋፅዎ ለማበርከት ይወስናል። ከልጅነቱ ጀምሮ ደስታ ይሰጠው የነበረውን እግር ኳስ ጨዋታ በበጎ ፍቃደኝነት የጎዳና ልጆችን ሰብስቦ ለመጫወትና ጎዳና ያሉትን አዳጊ ወጣቶች ለአጭር ጊዜም ቢሆን ለማስደሰት ከዛሬ ስምንት አመት በፊት ይወስናል። ያኔ እንደቀልድ የተጀመረው ስራ አድጎ ዛሬ ብዙ ወጣቶች ወደሚካፈሉበት የእግር ኳስ ፕሮጀክትነት ተቀይሯል ይላል ኤፍሬም፣ ኤፍሬም ይህንን በበጓ ፍቃደኝነት የሚያደርገውን ስራ ሲያከናውን ፈተናዎችም ገጥመውታል።  የወደፊት ትልቅ አላማም አለው።  የወጣቶች ማዕከል ማቋቋም ይፈልጋል። አጫውቶናል። ሁሉንም ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic