ኤድስ | በማ ድመጥ መማር | DW | 14.01.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

በማ ድመጥ መማር

ኤድስ

ዝግጅታችን በኤች አይ ቪ መያዝ ስለሚያስከትለው ችግርና ከቫይረሱ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል መሳጭ የሆኑ መረጃዎችን ያቀርብላችኋል።

default

ኤድስ

ስርጭቱን መከላከል

በኤች አይ ቪ ላይ ያተኮሩ የቅርብ ጊዜ ዜናዎች ለአፍሪቃ ጥሩ ተስፋዎች ናቸው። በስርጭቱ ክፉኛ በተጎዱ አንዳንድ የአፍሪቃ አገሮች የበሽታው መጠን እየቀነሰ መጥቷል። ሆኖም ግን የስርጭቱ መጠን ዛሬም ከየትኛውም የዓለማችን ክፍሎች አፍሪቃ ውስጥ ከፍተኛ ነው። በመላው ዓለም ካሉ የኤች አይ ቪ ሰለባዎች ወደ ሰባ ከመቶ የሚጠጉት አፍሪቃ ውስጥ ይኖራሉ።

እንደተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ከሆነ በየዓመቱ ወደ ሁለት ሚልዮን የሚጠጉ አፍሪቃውያን በኤች አይ ቪ ቫይረስ መዘዝ ይሞታሉ። የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች በተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች እየተካሄዱ ነው። ይሁንና ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ያሉት የተሳሳቱ ግምቶች አሁንም አልጠፉም። ለምሳሌ ብዙ ወንዶች ከግብረ-ስጋ ግኑኝነት በኋላ በሙ ቅ ውሃ በመታጠብ እንዲሁም ሚጥሚጣ በመብላት ኤድስን መከላከል ይቻላል ብለው ያምናሉ።

የመገለል ፍርሃት

ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩትን ማግለል ትልቅ ችግር ሆኖ ቀጥሏል። በርካታ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖች ከቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው ሊደርስባቸው የሚችል መገለልን በመፍራት ራሳቸውን ይደብቃሉ። ግን ኤች አይ ቪ ኤድስ የሞት ፍርድ አይደለም። አንድ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከኤች አይ ቪ ጋር ተያይዘው የሚመጡ በሽታዎችን የሚከላከሉ መድሃኒቶችን በአግባቡ በመጠቀም የተሻለ ሕይወት ሊኖረው ይችላል።

በማዳመጥ መማር

ከበማዳመጥ መማር ዝግጅት ዓላማዎች አንዱ በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ ያለውን የመረጃ እጥረት ማስወገድ ነው። ዝግጅታችን በኤች አይ ቪ መያዝ ስለሚያስከትለው ችግርና የመከላከያ ዘዴዎች ይዳስሳል። እንዲሁም ከቫይረሱና ቫይረሱ በደማቸው ከሚገኝ ሰዎች ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻል መሳጭ የሆኑ መረጃዎችን ያቀርብላችኋል። በሬድዮ የሚተላለፉ ዝግጅቶች ንድፈ-ሐሳባዊ የሆነ ደረቅ መረጃ ብቻ ናቸው ብሎ የሚጠብቅ ሰው ሊገርመው ይችላል። ዝግጅቶቻችን አስተማሪ ብቻ ሳይሆኑ አዝናኝ ጭምር ናቸውና።

በማድመጥ መማር የተሰኘው ዝግጅት በስድስት ቋንቋዎች ይቀርባል። ቋንቋዎቹም አማርኛ፣ ኪስዋሂሊ፣ ሃውሳ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛና ፖርቱጋልኛ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ ወይም ዝግጅቶቹን ለማዳመጥ ከፈለጉ እባክዎን www.dw-world.de/learning-by-ear የተሰኘውን ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።በማዳመጥ መማር የተሰኘው ፕሮጀክት በጀርመን ፌደራላዊ የውጪ ጉዳይ ሚ ኒስቴር ይታገዛል።

Audios and videos on the topic