ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ባለፈው ሳምንት ባቀረቡት ሪፖርት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት 28 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ማድረሱን ይፋ አድርገዋል። "ግጭት እና ጦርነት በነበረባቸው አካባቢዎች ሦስት ሚሊዮን ዜጎች ወደ ከፋ ድህነት" ገብተዋል። የበጀት ጉድለትና ያለቅጥ የሚሰፋው የክልሎች መዋቅር ያስከተለው ጫና በሪፖርቱ ከተካተቱ መካከል ናቸው
ሳፋሪኮም በአፍሪቃ በሞባይል ገንዘብ የማንቀሳቀስ አገልግሎት ስኬታማ የሆነውን ኤም-ፔሳ በኢትዮጵያ ሥራ ለማስጀመር ተዘጋጅቷል። የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተቀጥላ ሆኖ የተቋቋመው ኤም-ፔሳ ሞባይል ፋይናንሺያል ሰርቪስስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝቷል። ሳፋሪኮም ፈቃዱን እጁ ለማስገባት 150 ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በእጅ ስልኮች አማካኝነት ገንዘብ የማንቀሳቀስ አገልግሎት የሚሰጥበትን ኤምፔሳ ሥራ ለማስጀመር የሚችለውን ፈቃድ ከሁለት ቀናት በፊት ከብሔራዊ ባንክ ተቀብሏል። አገልግሎቱ ገንዘብ በቀላሉ እንዲዘዋወር፣ ቁጠባ እንዲበረታታ እና እንዲያድግ ብሎም በረጅም ጊዜ ሂደት ዜጎች የብድር አማራጭ እንዲያገኙ እድል የሚያሰፋ ስለመሆኑ ተገልጿል።
ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ ያለበት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 100 ሚሊዮን ብር ገደማ ማትረፉን አስታውቋል። በመስከረም 2013 የተቋቋመው ኩባንያ አመራሮች ማሻሻያ ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑን ቢናገሩም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተደረገ ውይይት ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከቀድሞው ሜቴክ ችግሮች እምብዛም እንዳልተላቀቀ ጠቁሟል
አንገብጋቢ የሠራተኞች ጥያቄ ለመንግሥት የሚቀርብበት የሜይ ዴይ ሰልፍ ከተሰረዘ በኋላ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ከአባላቱ ጋር በቀጣዩ እርምጃ ላይ ለመወያየት ተዘጋጅቷል። የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዝደንት ግን ችግሮች የበረቱበትን ሠራተኛ "ሁልጊዜ እሹሩሩ እያልን ልናሰራው አንችልም" ሲሉ መፍትሔ እንደሚያስፈልግ ይሞግታሉ
ከሰኞ ሚያዝያ 16 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በበይነመረብ ክፍያ ሥርዓት ብቻ እንዲከናውን የወጣው መረኃ ግብር ተጠቃሚዎችን እያማረረ ነው ። አሽከርካሪዎች የበይነ መረብ መንቀርፈፍ እና መጓተት ላልተፈለገ ረዥም ሰልፍ እየዳረጋቸው መሆኑን ጠቅሰዋል ።
የዕለቱን ዝግጅት ለማዳመጥ «የቀጥታ ሥርጭት ማድመጫ» የሚለውን ማገናኛ ይጫኑ
በኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ በየቀኑ የሚቀዳው እያንዳንዱ ስኒ ቡና፥ በተለይ ሴቶች ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ በማድረጉ ረገድ በምጣኔ ሀብቱ ላይ ትንሽም ቢሆን የሚፈይደው ነገር አለ።