ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
አብዛኛውን ጊዜ ሰውነት ለኢቦላ ተሐዋሲ ከተጋለጠ በኋላ የበሽታው ምልክቶች ከስምንት እስከ እስር ቀናት ባሉት ጊዜያትም መታየት ይጀምራሉ።
ተሐዋሲው አለ ተብሎ ሲጠረጠር በቅድሚያ በፍጥነት ሐኪም ማናገር ይገባል።
የኢቦላ ተሐዋሲ በዓይን የማይታይ ንዑስ ነቁጥ ነው። በአጉሊ መነጽር ሲታይ ግን ጫፉ እንደመቋጠር ያለ ክር አይነት ቅርጽ ያለው ይመስላል።
ምንም እንኳን ለኢቦላ ተብሎ በተለይ የተሰራ መድኃኒት ባይኖርም በሽታው በቶሎ ህክምና ካገኘ የኅመምተኛው ሕይወት የመትረፍ ዕድል ከፍተኛ ነው።
ኢቦላ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍባቸው መንገዶች እንደ ደም፣ ምራቅ፣ ላብ ወይንም የወንድ የዘር ፈሳሽ ባሉ ከሰውነት ከሚወጡ ፈሳሾች ጋር ንክኪ በመፍጠር ነው።
የኢቦላ በምዕራብ አፍሪቃ መቀስቀስና በፍጥነት መስፋፋት አብዛኛውን ጊዜ ተጨባጭ ባልሆኑ፥ ሊቀለበሱ በማይችሉ ቅድመ-ብይኖች እና ፍራቻዎች የታጀበ ነው።
በኢቦላ የተጠቁ ሰዎች ከሞቱ በኋላ የተሐዋሲው ዋነኛ አስተላላፊዎች በመሆናቸው አስክሬናቸው መነካት የለበትም። ሥርዓተ ቀብር መፈፀም ያለበት በሠለጠኑ ባለሙያዎች ነው።
የኢቦላ ተዛማች በሽታን ተቋቁመው የተረፉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ መገለል እና አድልዎ ይገጥማቸዋል። ብዙዎቹ ከዚህ በሽታ የተረፉ ሰዎች ወዳጆቻቸው ከእነሱ ጋር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይፈልጉ ይገነዘባሉ፤ አንዳንዶቹ እንደውም ሥራቸውን ሁሉ ያጣሉ። ይኽ ተገቢ አይደለም።