ኤቦላ እና የዓለም አቀፉ ምላሽ | ዓለም | DW | 04.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ኤቦላ እና የዓለም አቀፉ ምላሽ

በምዕራብ አፍሪቃ የተከሰተውን የኤቦላ ስርጭት ለማብቃት የተደረገውን ዘመቻ ለመገምገም ትናንት በብራስልስ የተጠራው ዓለም ስብሰባ በበሽታው የተጎዱት ሀገራት ውስጥ የተኀዋሲው ስርጭት በጠቅላላ እስኪያቆም ድረስ መቀጠል እንዳለበት አሳሳበ።

ለጋሽ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም ርዳታቸውን እና ድጋፋቸውን መስጠት እንዲያሳድጉ ተማፅኖዋል። ኤቦላ ከተከሰተ ካለፈው አንድ ዓመት ተኩል ውስጥ ወደ አስር ሺህ የሚጠጉ ሰዎች መሞታቸው፣ 24,000 ደግሞ ለወረርሽኙ እና ወረርሽኙ ላስከተለው ኤኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር መጋለጣቸው ተገልጾዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic