ኤቦላ እና የኤኮኖሚ ተፅእኖው | ኤኮኖሚ | DW | 26.08.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

ኤቦላ እና የኤኮኖሚ ተፅእኖው

የኤቦላ ተኀዋሲ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ በሽታው በዋነኝነት በተስፋፋባቸው በላይቤሪያ ሴራልዮን ና ጊኒ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲገታ አድርጓል ።

በምዕራብ አፍሪቃ እየተስፋፋ የሄደው ኤቦላ በአጭር ጊዜ ካልተገታ የማህበራዊና የኤኮኖሚ ቀውስ በማስከተል በሽታው የተዛመተባቸውን ሃገራት መንግሥታት ከፍተና ችግር ውስጥ እንደሚጥል እየተገለፀ ነው ። የኤቦላ ተኀዋሲ በንክኪ የሚተላለፍ በመሆኑ በሽታው በዋነኝነት በተስፋፋባቸው በላይቤሪያ ሴራልዮን ና ጊኒ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲገታ አድርጓል ። ሶስቱ ሃገራት ድንበራቸውን የዘጉ ሲሆን ወደ እነዚህ ሃገራት የሚደረጉ በረራዎችም ለጊዜው ቆመዋል ። ይህም የሃገራቱን የቱሪዝምና የንግድ ኢንዱስትሪ በእጅጉ አዳክሟል ።በማዕድን ማውጣትና በልዩ ልዩ የኤኮኖሚ ዘርፎች የተሠማሩ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸውን ማስወጣታቸው ወይም እንዳይገቡ ማድረጋቸው በሃገራቱ ኤኮኖሚ ላይ ጫና ፈጥሯል ።ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic