ኤቦላ እና የአውሮጳ ኅብረት ርዳታ | ጤና እና አካባቢ | DW | 30.09.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ኤቦላ እና የአውሮጳ ኅብረት ርዳታ

በምዕራብ አፍሪቃ እየተስፋፋ የመጣውን አደገኛዉን የኤቦላ ወረርሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥረቱ እንደቀጠለ ነው። ጀርመን በኤቦላ ተዋኅሲ ለተጠቁ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት አስር ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

ዩኤስ አሜሪካ በኤቦላ የተከሰተባቸው የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ወረርሽኙን ለመታገል በጀመሩት ዘመቻ ላይ የሚረዱ 3,000 ወታደሮችን እንደምትልክ ከፍተኛ የዋይት ሀውስ ቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት መግለጻቸው ይታወሳል። ወታደሮቹ ኤቦላ ወደተስፋፋባቸው ላይቤርያ፣ ሲየራ ልዮን እና ጊኒ በመሄድ በዚያ እያንዳንዳቸው 100 አልጋዎች የሚኖሩዋቸው 17 ክሊኒኮችን በመገንባት እና እስከ 500 የሚጠጉ የጤና መኮንኖችን በማሠልጠኑ ተግባር ላይ እንደሚሠማሩ ተገልጾዋል።የኤቦላን ስርጭት ለመቆጣጠር በተጀመረው ጥረት ላይ የአውሮጳ ኅብረት አስተዋፅዖስ ምን ይመስላል?

ቤርንት ሪገርት

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic