ኤቦላን ለመታገል ተፈላጊው ዓለም አቀፍ ትብብር፣ | ጤና እና አካባቢ | DW | 09.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

ኤቦላን ለመታገል ተፈላጊው ዓለም አቀፍ ትብብር፣

ከላይቤሪያ የተመለሰው አሜሪካዊው የኢቦላ ሕመምተኛ ቶማስ ኤሪክ ዳንከን ትናንት በዳላስ ቴክስስ ካረፈ ወዲህ ይህን አደጋና በሽታ ለመታገልና ለመግታት ጠንካራ ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያሻ በመነገር ላይ ነው።

በምዕራብ አፍሪቃ ቢያንስ የ 3,800 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን አደገኛ በሽታ ለመታገል የሀኪሞች ርዳታ ፤ ተንቀሳቃሽ ክሊኒኮችና መሠረታዊ ሰባአዊ ርዳታ ምግብ ጭምር አስፈላጊ መሆኑ ተገለጠ። ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የሚጠበቀው ርዳታ የ 300 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደታየበት የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የገለጠ ሲሆን፤ የዓለም ባንክ፣ ኤቦላ ፣ እስከመጪው 2015 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ከቀጠለ የ 32 ,6 ቢሊዮን ዶላር ኪሣራ እንደሚያስከትል አስጠንቅቋል። አሜሪካዊው የኢቦላ ሕመማተኛ ትናንት ካረፈ ወዲህ ምን ዓይነት ስሜት ፈጥሮ ይሆን ? የዋሽንግተን ዲ ሲውን ዘጋቢአችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

አበበ ፈለቀ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic