1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«ኤስ ፔ ዴ» እጩ ተወዳዳሪ

ረቡዕ፣ ጥር 17 2009

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ፣ የ«ኤስ ፔ ዴ»  መሪ፣ ምክትል መራሔ መንግሥት እና የኤኮኖሚ ሚንስትር ዚግማር ጋብርየል በሚቀጥለው መስከረም ወር በሚካሄደው ፌዴራዊ ምክር ቤታዊ ምርጫ ላይ ፓርቲያቸውን በመወከል በመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል አንፃር እንደማይወዳደሩ ትናንት አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/2WOG7
Deutschland Martin Schulz bei der SPD Bundestagfraktion
ምስል picture alliance/dpa/K. Nietfeld

Ber. Berlin(SPD Kanzlerkandidat) - MP3-Stereo

በሳቸው ፈንታ ፓርቲውን ለድል የማብቃት እድላቸው የተሻለ ነው ያሏቸውን ጓዳቸውን እና የቀድሞው የአውሮጳ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ማርቲን ሹልስ  የ«ኤስ ፔ ዴ»  እጩ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀርቡ ሀሳብ አቅርበዋል። ጋብርየል የእጩ ተወዳዳሪውን ጥያቄ መልስ በሳምንቱ መጨረሻ ይካሄዳል በተባለ የፓርቲያቸው ስብሰባ ላይ ይፋ ያደርጉታል ተብሎ እየተጠበቀ ሳለ፣ ትናንት ድንገት ብዙዎች ከጠበቁት ለየት ያለ ውሳኔ መድረሳቸውን ማሳወቃቸው የፓርቲ ጓዶቻቸውን እና አባላትን ብቻ ሳይሆን በሃገሪቱ ብዙዎችን  አስገርመዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ