ኤርትራውያን ስደተኞች «ተገደው » ሁለተኛ የገቢ ቀረጥ ይከፍላሉ መባሉ | አፍሪቃ | DW | 09.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኤርትራውያን ስደተኞች «ተገደው » ሁለተኛ የገቢ ቀረጥ ይከፍላሉ መባሉ

በጀርመን ሀገር ከታወቁት ጋዜጦች አንዱ« ዚውድዶይቸ» ጋዜጣ ፣ ከሰሜን ጀርመን ፣ እንዲሁም፣ ከደቡብ ምዕራብ ጀርመን የራዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅቶች ጋር በመተባበር፤ አጣርተን ደርሰንበት ባሉት ዘገባ መሠረት በውጭ ተገን ጠይቀው የሚኖሩ ኤርትራውያን አከራካሪ የተሰኘ ድርብ ቀረጥ ወይም ግብር ይከፍላሉ።

በሌላ በኩል አሁን ገንዘብ በቀረጥ ስም ሳይሆን በሀገር ግንባታ ስም ኤርትራ ውስጥ በሚገኙ ወዳጆችና ዘመዶች በኩል እንዲሰጥ የሚደረግ መሆኑን ጋዜጣው የኤርትራን መንግሥት ባለሥልጣናት በመጥቀስ አስታውቋል። የምዕራባውያኑ ወቀሣ ለምን አሁን ጠንከር አለ? ለሀገር ግንባታ የሚከፍሉት ወገኖችስ ያሰቡትና የሚመኙት ነገር ይፈጸማል ወይ ? ዙድ ዶይቼ ጋዜጣ፤ ሁለቱ ራዲዮና ቴሌቭዝን ጣቢያዎች ኤርትርንና ኤርትራውያንን አመልክተው ስላቀረቡት ዘገባ ፣ የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃ/ሚካኤል----

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic