ኢጣልያ እና የስደተኞቹ ችግር | ዓለም | DW | 23.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ኢጣልያ እና የስደተኞቹ ችግር

ኢጣልያ ባለፉት 48 ሰዓታት ከ1,000 የሚበልጡ ስደተኞችን ማዳኗን የሀገሪቱ የባህር ኃይል ትናንት አስታውቋል። ከሰሜን አፍሪቃ ወደ አውሮPA ለመግባታ ሲሞክሩ የመስመጥ አደጋ የሚያሰጋቸውን ስደተኞች ለማዳን ባለፉት ጊዚያት አንዳንድ ድርጅቶች ተቋቁ መው እየተንቀሳቀሱ ነው።

ይሁንና፣ ስደተኞቹን የማዳኑ ተግባር ከቀኝ ክንፍ ፓርቲዎች ብርቱ ወቀሳ ተፈራርቆበታል። ይኸው የማዳን ተግባር ግን ብዙ ወጪ የሚጠይቅ ነው በሚል አሁኑኑ እንዲቆም ጠይቀዋል። ብራስልስ የሚገኘው የስደተኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት ስደተኞቹን የማዳኑ ተግባር መቋረጥ እንደማይገባው በማስታወቅ ፣ ስደተኞቹን የማዳኑ እና የመቀበሉ ተግባር የሚጠይቀውን ወጪ ኢጣልያ ብቻ ሳትሆን ሌሎችም አውሮጳውያት ሀገራት ሊካፈሉት እንደሚገባ አሳስቦዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic