1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢጋድ እና ስደተኞች 

ረቡዕ፣ መስከረም 7 2012

የአውሮጳ ህብረት ፣የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በምህጻሩ ኢጋድ አባል ሃገራት«የራስን ችግር በራስ መፍታት»በሚለው መርህ ስደተኞችን መውሰድ የጀመሩበትን አሰራር እንደሚደግፍ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3Pp5G
Äthiopien | Igad-Ministertreffen zur Erklärung von Nairobi
ምስል DW/G. Tedla

የአውሮጳ ህብረት ፣የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት በምህጻሩ ኢጋድ አባል ሃገራት«የራስን ችግር በራስ መፍታት»በሚለው መርህ ስደተኞችን መውሰድ የጀመሩበትን አሰራር እንደሚደግፍ አስታወቀ።የናይሮቢ መርሃ ግብር በሚባለው በዚሁ ጥረት ላይ የኢጋድ አባል ሃገራት ተጠሪዎች እና የዘርፉ ባለሞያዎች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የተገኙት የህብረቱ ተጠሪ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ህብረቱ ጥረቱን ለመደገፍ ወደ ኃላ ብሎ እንደማያውቅ እና ወደፊትም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።በዚሁ ስብሰባ ላይ አባል ሃገራትም ሆኑ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።


ጌታቸው ተድላ
ኂሩት መለሰ   

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ