ኢጋድ በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 13.12.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢጋድ በኢትዮጵያ

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት /ኢጋድ/  አባል ሃገራት መሪዎች ባለፈዉ ቅዳሜ አዲስ አበባ ላይ ተገናኝተዉ አሁን በሶማሊያና በደቡብ ሱዳን ያለዉ የፖለቲካ ቀዉስ ላይ መወያየታቸዉን የደርጅቱ ኮሙኒኬሼን ኃላፊ ማሀመድ አህሜድ ለዶቼ ቬሌ የላኩት መግለጫ ያመለክታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:42
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:42 ደቂቃ

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት

ኢጋድ በደቡብ ሱዳን የሰዉ ህይወት መጥፋትና የንብረት መዉደም እንዲሁም አሸባብ በሶማሊያ መንግሥትና በማኅበረሰብ ላይ የሚያደረሱትን ጥቃት እንደሚያወግዝ መግለጫዉ ይጠቅሳል።

ድርጊቱን ከማዉገዝ በበለጠ በመሬት ላይ የኢጋድ ሥራ ምን ይመስላል? ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በስክል ወደኢጋድ ዋና ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ቢሮዎች በተደጋጋሚ ብንደዉልም አልተሳካልንም። ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነትና ስልታዊ ጥናት ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑትና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት አበበ አይነቴ በደቡብ ሱዳን የኢጋድን ተጨባጭ እንቅስቃሴ ግድፈቶች ብኖሩትም ንቁ ስራዎችን ኢየሰራ ነዉ ይላሉ። 

ስብሰባዉ የተካሄደባት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፖለቲካ አለመረጋጋት በመከሰቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ትገኛለች። እንዲያም ሆኖ የኢጋድ መሪዎች በስብሰባቸዉ የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፓለቲካ ጉዳይ አስመልክተዉ ስለ መወያየታቸዉ የተሰማ ነገር የለም።

«የኢጋድ አባል አጋሮች የየትኛዉም አገር የዉስጥ ጉዳይ ላይ ታልቃ አለመግባት» እንደ ዋና መርህ ቢይዝም የኢጋድ መሪዎች  በተለይ ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች ትኩረት አልሰጡም በሚል ይተቻሉ። ይሁን እንጂ አቶ አበበ ይህ ትችት ዉኃ አይቋጥርም ነዉ የሚሉት።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ደረ ገጽ ተከታታዮቻችንን አስተያየታቸዉን ጠይቀን ነበር። «የራሳችንን ሰላም እኛዉ እራሳችን እንጠብቃለን። ከዉጭ የሚመጣ አካል ወይም ፅንፈኛ ዲያስፖራዎች ለሀገራችን ፀረ ሰላም ናቸዉ፤» የሚል አስተያየት የሰጡ አሉ። ሌሎች ደግሞ «የአፍሪቃ መሪዎች ለአፍሪቃዊ ህዝባቸው ጠላት ናቸው። በተለይ ኢጋድ፣ እነሱ የሚጨነቁት እንዴት አወናብደው በሰልጣናቸው እንደሚቆዮ ብቻ ነው። አፍሪቃውያን በራሳቸዉ ልጆች እየተገደሉ ደማቸው እየፈሰሰ ፍዳ እያዩ ነው። የኛም ለዚህ ትልቅ ምሳሌ ነው፣» በማለት አስተያየታቸዉን አጋርተዋል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሠ 


 

Audios and videos on the topic