ኢድ አልፈጥር በሳውዲ እና አሜሪካ | ዓለም | DW | 06.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ኢድ አልፈጥር በሳውዲ እና አሜሪካ

1437ኛዉ የኢድ አልፈጥር በዓል በሳውዲ አረብያ በተለመደው ስርዓት የተከበረ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም በተመሳሳይ በአሉን አክብረዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:04

ኢድ አልፈጥር

በረመዳን የፆም ወራት የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በደረሰባት በሳዉዲ በመካና በመዲና ከሳዑዲ አረቢያና ከመላው ዓለም የተወጣጡ አንድ መቶ ያህል የሀገር መሪዎችና ታላላቅ ሰዎችን ጨምሮ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች የዑምራ ስርአት አከናውነዋል፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ የጸጥታና የደህንነት ምንጮች የዘንድሮው የዑምራ ስርዓትና የኢድአልፈጥር በዓል ሰላማዊ ሊባል የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል። ከዑምራ መልስ ባጋጠሙ ሁለት የመኪና አደጋዎች የሰባት ኢትዮጵያዊያን ሕይወትማለፉ ተገልጧል። በዋሽንግተን ዲሲእና አካባቢዋ ወደ350,000 አሜሪካዊ የሙስሊም ማኅበረሰብ እንደሚኖር ይነገራል። ከእነዚህ ውስጥ ወደሃያ አምስት ሺህ የሚጠጉት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሆናቸው ይጠቀሳል። ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች በዓሉን የሚያከብሩት ለተቸገረው ወገናቸው ወደ8 ሺህ ዶላር፤ በድርቅ ለተጎዱት ደግሞ 5 ሺህ ዶላር አዋጥተው በመስጠት ነው።

ስለሺሽብሩ/ መክብብ ሸዋ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic