ኢትዮ-ጀርመናዊዉ የአቶም ሳይንቲስት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ኢትዮ-ጀርመናዊዉ የአቶም ሳይንቲስት

ፈረንሳይና ብሪታኒያን የመሳሰሉ ሃገሮች ግን የአቶም ኃይል ጣቢያዎቻቸውን የመዝጋትም ሆነ የመቀነሰ ሃሳብ የላቸውም ። አንዳንድ የአፍሪቃ ሃገሮች ደግሞ የአቶም ቴክኖሎጂን የመጠቀም ፍላጎት እያሳዩ ነው ። ዶክተር ጌድዮን ግን የአቶም ቴክኖሎጂን መጠቀምን ለአፍሪቃ አገራት አይመክሩም ።

የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ፣ እዚህ ጀርመን ፣ በአቶም ሳይንስ መምህርነትና ተመራማሪነት በሚያገለግሉት በዶክተር ጌድዮን ጌታሁን ሥራና ተሞክሮ ላይ ያተኩራል ። ዛሬ የሚቀርበው 2 ተኛ ክፍል ዝግጅት ውስጥ ከተካተቱት ነጥቦች መካከል የአቶም ኃይልና አፍሪቃ እንዲሁም የሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር ለማሳደግ መከናወን ያለባቸው ተግባራት ይገኙበታል ።
የራድዮ ኬሚስትሪና የኒዩክልየር ኬሚስትሪ ምሁሩ ዶክተር ጌድዮን ጌታሁን እጎአ ከ1995 አም አንስቶ በማይንዙ የዮሐንስ ጉትንበርግ ዩኒቨርስቲ የአቶም ሳይንስ ተቋም ውስጥ ነው የሚሰሩት ። ከ2009 አም አንስቶ በዚሁ ተቋም ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው ። ከ 2012 ወዲህ ደግሞ ከዚሁ ሥራቸው በተጨማሪ በዳርምሽታት ዩኒቨርስቲ የአቶም ኃይልን አስተማማኝነት ለማወቅ በሚደረግ ምርምር ውስጥ ከሌሎች ባለሞያዎች ጋር እየሰሩ ነው ። ዶክተር ጉድዮን እንዳሉት ዝንባሌያቸው ወደ ሳይንስ ትምህርት የሆነው ገና የ7 ተኛ ክፍል ተማሪ አንስቶ ሳሉ ነው ። የያኔው የሳይንስ አስተማሪያቸው በመከሩዋቸው መሰረት በዚሁ ትምህርት ለመግፋት ወስነው የዛሬ 39 አመት ጀርመን መጡ ። ብዙዎች ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዘኛ ተናጋሪ ሃገር በሚሄዱበት በዚያን ዘመን የወጣቱ ጌድዮን ምርጫ ጀርመን የሆነበት ምክንያት ምን ይሆን ? ዶክተር ጌድዮን

Johannes Gutenberg-Universität Mainz, Forum, eingestellt am 22.12.2009, Foto: Hartmann Fotodesign


ዶክተር ጌድዮን ሽቱትጋርት ኬምስትሪ ተምረው እዚያው ጥቂት ሰርተው ደግሞ ዳርምሽታት ከተማ የኬሚካል ኢንጅነሪንግ ትምህርት ካጠኑ በኋላ በብሪታኒያው የላስፕሮ ዩኒቨርስቲ በአቶም ሳይንስ በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀው ጀርመን በመመለስ በማይንዙ የዪሐንስ ጉትንበርግ ዩኒቨርስቲ የአቶም ሳይንስ ተቋም ውስጥ ሥራ አገኙ ። ዶክተር ጌድዮን የዛሬ 39 አመት የመጡባት ጀርመን እጎአ ከ1957 ጀምሮ የአቶም ኃይልን ትጠቀማለች ። ዶክተር ጌድዮን እንደተናገሩት ከ1957 እስከ 2004 አመተ ምህረት በጀርመን 110 የአቶም ጣቢያዎች ነበሩ ከ 1958 እስካሁን ድረስ ደግሞ 45 የሚሆኑ የምርምር ጣቢያዎች ነበሩ ። ከነዚህ ሁሉ ግን አሁን 21 ተዘግተው 15ቱ ደግሞ እየታደሱ ነው ። በተለይ ጃፓን ፉክሽማ ውስጥ ከደረሰው የአቶም ኃይል መስጫ ጣቢያ አደጋ በኋላ ጀርመን የአቶም ኃይል ጣቢያዎቿን ቀስ በቀስ እንዲከስሙ በማድረግ ላይ ናት ። በአሁኑ ሰአት አገልግሎት የሚሰጡት 7 የኒዩክልየር ምርምር ጣቢያዎችና 9 የኃይል አመንጪ የአቶም ጣቢያዎች ብቻ ናቸው እንደ ዶክተር ጌድዮን ። ምንም ጀርመን ይህን መሰሉን እርምጃ ብትወስድም ፈረንሳይና ብሪታኒያን የመሳሰሉ ሃገሮች ግን የአቶም ኃይል ጣቢያዎቻቸውን የመዝጋትም ሆነ የመቀነሰ ሃሳብ የላቸውም ። አንዳንድ የአፍሪቃ ሃገሮች ደግሞ የአቶም ቴክኖሎጂን የመጠቀም ፍላጎት እያሳዩ ነው ። ዶክተር ጌድዮን ግን የአቶም ቴክኖሎጂን መጠቀምን ለአፍሪቃ አገራት አይመክሩም ።

Johannes Gutenberg-Universität Mainz, Hauptportal, eingestellt am 22.12.2009 Foto: Hartmann Fotodesign


ዶክተር ጌድዮን ጌታሁን በአርሲ ክፍለ ሃገር አቦምሳ አውራጃ መርቲ ወረዳ ነው የተወለዱት ። አባታቸው ቀኝ አዝማች ጌታሁን መሸሻ ለያኔው የኢትዮጵያ የህግ መምሪያ ምክር ቤት ተመርጠው ወደ አዲስ አበባ በመምጣታቸው
1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአቃቂ አድቬንቲስት ሚስዮንና በበየነ መርዕድ ትምህርት ቤቶች የ2 ተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በያኔው አጠራር በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው ያጠናቀቁት ። ሳይንቲስቱ ዶክተር ጌድዮን በሊቀመንበርነት ባገለገሉበት በራይንላንድፋልስ ውስጥ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሐኪሞችና መሐንዲሶች እንዲሁም የስነ ፍጥረት ባለሞያዎች አንድነት ማህበር አማካይነት ኢትዮጵያ የሚገኙ የሳይንስ ተቋማትን ምሁራንን ተማሪዎችን ይረዳሉ ። በኢትዮጵያ የሳይንስ ተቋማትም ሆነ የሳይንስ ተማሪዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑን ዶክተር ጌድዮን ይናገራሉ ዶክተር ጌድዮን ምክንያቱን ጀርመን ካለው ልምድ ጋራ በማነፃፀር ይገልፃሉ ።
ዶክተር ጌድዮን ተማሪዎች የኬሚስትሪ ትምህርት ፍላጎት እንዲያድርባቸው መከናወን አለባቸው ያለባቸውን ተግባራትም ጠቅሰዋል ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ