ኢትዮ-ኤርትራ፣ ኤሌክትሪክ እንደ መደራደሪያ? | ኢትዮጵያ | DW | 01.08.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮ-ኤርትራ፣ ኤሌክትሪክ እንደ መደራደሪያ?

ኢትዮጵያ የኤርትራን መንግስት ወደሰላማዊ የድርድር መድረክ ለማቅረብ 250 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል በነጻ ለመስጠት አስባለች መባሉንየሚጠቁም ዜና በድረገጾች እየተነበበ ነዉ።

default

የኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርን በስም በመጥቀስ የቀረበዉ ዘገባ፣ በሎንዶን ለሚገኙ የኤርትራ ማኅበረሰብ ንግግር አሰሙ ያላቸው ኤርትራዊ ሚንስትር ሁለቱ ሃገሮች ወደጤናማ ግንኙነት የሚገቡት ኢትዮጵያ በኃይል ከያዘቻቸዉ የኤርትራ ግዛቶች ስትለቅ ነዉ ማለታቸዉን ያትታል። የኢትዮጵያ መንግስት ዘገባዉን አስተባብሏል፤ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የሚመለከታቸዉን የመንግስት አካላት በማነጋገር ዘገባ ልኮልናል። የተሰራጨዉን ዘገባ በመጥቀስ ወደአስመራ ደዉለን ያነጋገርናቸዉ በኤርትራ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ ጸሀዬ ፋሲልም የተጀመረ ድርድርም የለም የኤሌክትሪክ ኃይል የመስጠት ሀሳብ ቀርቦዋል ስለመባሉም መንግስታቸዉ የሚያዉቀዉ እንደሌለ ገልጸዉልናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic