ኢትዮ ኑረንበርግ ስለ ሮሙ ውድድር | ስፖርት | DW | 25.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

ኢትዮ ኑረንበርግ ስለ ሮሙ ውድድር

15ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባሕል ፌስቲቫል ከነገ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ድረስ በጣሊያን መዲና ሮም ከተማ ውስጥ ይከናወናል። ፌዴሬሽኑ ውስጥ በተነሳ አለመግባባት ግን ዘንድሮ በሮሙ ዝግጅት የሚሳተፉ የጀርመን ቡድኖች ሁለት ብቻ ናቸው፤ ኢትዮ ሽቱትጋር እና ኢትዮ ፍራንክፉርት ቡድኖች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:10

የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባሕል ፌስቲቫል ከረቡዕ እስከ ቅዳሜ ድረስ በሮም

15ኛው በአውሮጳ የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባሕል ፌስቲቫል ከነገ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ድረስ በጣሊያን መዲና ሮም ከተማ ውስጥ ይከናወናል። ፌዴሬሽኑ ውስጥ በተነሳ አለመግባባት ግን ዘንድሮ በሮሙ ዝግጅት የሚሳተፉ የጀርመን ቡድኖች ሁለት ብቻ ናቸው፤ ኢትዮ ሽቱትጋር እና ኢትዮ ፍራንክፉርት ቡድኖች። ኢትዮ ኮሎኝ ቡድን ትናንት ባቀረብነው የስፖርት ዝግጅት እንደገለጠው በውድድሩ የማይሳተፈው ፌዴሬሽኑ ውስጥ አለ ያለው ግልጽ ያልሆነ አሠራር የጠራ ባለመሆኑ ነው።

ፌዴሬሽኑ ለቀረቡበት ቅሬታዎች በትናንትናው የስፖርት ዝግጅታችን ምላሽ ሰጥቷል። የኢትዮ ኑረንበርግ የስፖርትና የባሕል ማኅበር ቡድን አባል አቶ ሳምሶን ተሰማ ቡድናቸው ለምን በሮሙ ዝግጅት እንደማይሳተፍ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። ማንተጋፍቶት ስለሺ አነጋግሯቸዋል።  
 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች