ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹን ይቅርታ ጠየቀ | ኢትዮጵያ | DW | 18.06.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞቹን ይቅርታ ጠየቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ከሰኔ 3 ቀን 2011 ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት በመላ ሃገሪቱ በከፊልና ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠየቀ። ኢትዮ ቴሌኮም በFB ባወጣዉ አጭር የጽሑፍ መግለጫ እንደገለፀዉ የጥቅል አገልግሎት እና የፕሬሜር አገልግሎት ገዝተዉ መጠቀም ያልቻሉ ብሎአል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከሰኔ 3 ቀን 2011 ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት በመላ ሃገሪቱ በከፊልና ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠየቀ። ኢትዮ ቴሌኮም በFB ባወጣዉ አጭር የጽሑፍ መግለጫ እንደገለፀዉ የጥቅል አገልግሎት እና የፕሬሜር አገልግሎት ገዝተዉ መጠቀም ያልቻሉ፤ አገልግሎቱ ሲከፈት መጠቀም እንደሚችሉ አስታዉቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ላለፉት ስምንት ቀናት ኢትዮጵያ አብዛኛዉ ክፍል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት ዛሬ ዘግቦአል። እንደ ዜና አገልግሎቱ  በሃገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ለምን እንደተቋተጠ በይፋ የተገለፀ ነገር የለም።  የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ምንጮች ለዜና አገልግሎቱ እንደገለፁት ከአዲስ አበባ ከተማ በስተቀር በአብዛኛዉ የኢትዮጵያ ከተሞች የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬም ተቋርጦ ነዉ የዋለዉ። የቴሌኮሙ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ኃላፊ ጨረር አክሊሉ በሃገሪቱ በአብዛኛዉ ክፍሎች የኢንተርኔት አገልግሎት ለምን እንደተቋረጠ ዝርዝር መግለጫ ከመስጠት መቆጠባቸዉንና ፤ አገልግሎቱ በምን ምክንያት እንደተቋረጠ የሚገልፅ መግለጫ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ይፋ እንደሚደረግ ወጣና እንስከዛዉ ተጠቃሚዎች በትግዕግስት እንዲጠብቁ መናገራቸዉን  አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቦአል። ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎት ሲቋረጥ የአሁኑ የመጀመርያዉ ነዉ። እንድያም ሆኖ ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የሚሰጠዉን የመልቀቅያ ፈተና ተከትሎ መቋረጡንና ብሔራዊዉ ፈተና የፊታችን አርብ መጠናቀቁን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ዳግም ይፋ ይሆናል ተብሎ አንደሚጠበቅ ተመልክቶአል። በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃዉሞ በነበረበት ወቅት ከጎርጎረሳዉያኑ 2015 እስከ 2017 ለተደጋጋሚ ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎት ይቆራረጥ እንደነበር ዜና ምንጩ አስታዉሷል።

 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ