ኢትዮ ቴሌኮም ምስጋናና የደንበኞች ስሞታ | ኢትዮጵያ | DW | 11.07.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮ ቴሌኮም ምስጋናና የደንበኞች ስሞታ

ኢትዮ ቴሌኮም የአዲስ በጀት ዓመትን መጀመር አስመልክቶ ደንበኞችን ለማመስገን ለሦስት ቀናት የሚቆይ የኢንተርኔት ፣ የአጭር የጽሁፍ መልእክት እና የድምጽ አገልግሎት በመስጠት፤ ወደፊትም ይህን አሰራር ተግባራዊ ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም የአዲስ በጀት ዓመትን መጀመርን አስመልክቶ ደንበኞቹን ለማመስገን ለሦስት ቀናት የሚቆይ የኢንተርኔት ፣ የአጭር የጽሁፍ መልእክት እና የድምጽ አገልግሎት በመስጠት፤ ወደፊትም ይህን አሰራር ተግባራዊ ማድረጌን እቀጥላለሁ ብሏል።  ከሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ አንስቶ እስከ ትናንት ረቡዕ የቆየውን የቴሌ ስጦታ አስመልክቶ ዶይቼ ቬለ «DW» ያነጋገራቸው ደንበኞች እንደሚሉት ደግሞ ስጦታው መልካም ቢሆንም በተለይ የኢንተርኔት አገልግሎቱ ይህንን አደረግሁ ለማለት እና የህዝብ ግንኙነት ሥራ ለመሥራት ካልሆነ በቀር  ጥራቱ  የተለመደው አይነት ነው ብለዋል። «Facebook» እና «youtube »መጠቀም አላስቻለንም ያሉት የኢንተርኔት አቅርቦት ነጻ አገልግሎት ሰጠን መባሉ ትርጉም ያለው ነገር አይደለም ሲሉም ተችተዋል። የቴሌኮም የነጻ አገልግሎት 1 ጊጋ ባይት የኢንተርኔት፣ የ20 ደቂቃ የሀገር ውስጥ የስልክ ጥሪ እንዲሁም 30 የሀገር ውስጥ አጭር የጽሑፍ መልእክትን ያካተተ ነው። ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ የተጠቃሚዎችን አስተያየት በማካተት አጭር ዘገባ ልኮልናል። 

ሰሎሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሰ   

Audios and videos on the topic