ኢትዮጽያ የኤሌትሪክ ሃይል ይዞታና የተያዘዉ እቅድ | ኢትዮጵያ | DW | 15.01.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጽያ የኤሌትሪክ ሃይል ይዞታና የተያዘዉ እቅድ

ኢትዮጽያ ከሶስት ወራት በፊት የተከዜ ሃይል ማመንጫ ግድብን ማጠናቀቋ፣ ግድቡ በሙሉ ሃይል ስራ ላይ ሲዉል ሶስት መቶ ሜጋ ዋት ሃይል እንደሚያመነጭ ተገልጾአል።

default

አገሪቷ የሃይል ምንጯን ከራስዋ አልፋ ለጎረቤት አገሮች ብሎም ለአዉሮጻ ለመሸጥ ማቀድዋ ሊሆን የሚችል ነዉን?

ሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የግልገል ግቤ የሃይል ማመንጫ ተጠናቆ መመረቁም ይታወቃል። በመቀጠል ከሁለት ወራት በኻላ ከበለስ የሃይል ማመንጫ አራት መቶ ሜጋ ዋት ሃይል ማመንጨት እንደሚቻልም ተገልጾአል። የሃይል ምንጭ ግድቦች ተሰርተዉ መጠናቀቅ በአገሪቱ ተፈጥሮ የነበረዉን የሃይል እጥረት በማማሏት ኢኮነሚዉን እንደሚያነቃቃዉ ሲገለጽ በሌላ በኩል ምርጫዉ በሚደረግበት አመት የግድቡ መመረቅ ገዥዉ ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ ሊጠቀምበት ፈልጎ ነዉ ተብሏል። አገሪቷ የሃይል ምንጯን ከራስዋ አልፋ ለጎረቤት አገሮች ብሎም ለአዉሮጻ ለመሸጥ ማቀድዋ ደግሞ በመነገር ላይ ነዉ። ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችል ነዉን? ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ በኢትዮጽያ የኢሌትሪክ ሃይል ዙርያ በኢትዮጽያ ሳምንታዊ የኢኮነሚ ጋዜጣ አዘጋጅ እና ባለቤትን አነጋግሮ ይህን አጠናቅሮልናል።
ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ