ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር | ኢትዮጵያ | DW | 11.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ 26 ዓመታት በኢህአዴግ አመራር

የደርግን ሥርዓት የተካዉ ህወሀት መራሹ ኢሕአዴግ ሥልጣን የያዘበት 26ኛ ዓመት ባለፈዉ ግንቦት ሃያ ተከብሯል። ኤሕአዴግ ሥልጣን እንደያዘ የሕዝቡን የፖለቲካና ማኅበራዊ ችግሮች ለማስወገድ መቁረጡን ገልጾ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:00

ዛሬም ለመብቶች፤ ለሕግ የበላይነት የሚጮኽባት ሀገር፤

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ መሠረታዊ መብቶች መከበራቸዉን የሚደነግገዉን ሕገ መንግሥት ከማጽደቅ አንስቶ፤ በፖለቲካዊም ሆነ በኤኮኖሚዉ ዘርፍ ቀላል የማይባሉ ተግባራት መከናወናቸዉን ብዙዎች ይስማሙበታል። ለዉጦቹ ተስፋ ሰጪ ሆነዉ አለመቀጠላቸዉ ግን ወትሮ ይነሱ የነበሩ የሰብዓዊ መብቶች መከበር፣ የመድበለ ፓርቲ ምሥረታ፤ የሕግ የበላይነት ወዘተ ጥያቄዎች ዛሬም እንዲያስተጋቡ ምክንያት እንደሆኑም በሰፊዉ ይታመናል። ኢትዮጵያ አሁን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ትገናለች። ሌላስ?   ለ26 ዓመታት በኢህአዴግ የምትተዳደረዉ ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች? ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ አድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic