ኢትዮጵያ፤ የፍርድ ሒደትና የመንግሥት ፊልሞች | እንወያይ | DW | 21.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

እንወያይ

ኢትዮጵያ፤ የፍርድ ሒደትና የመንግሥት ፊልሞች

የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠረዉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፈዉ ጥር ሃያ-ስምንት ጀሐዳዊ ሐረካት በሚል ርዕሥ ያሰራጨዉ ፊልም የብዙዎችን ተቃዉሞ፥ የጥቂቶችን ቅሬታ፣ ጥያቄ አስከትሏል።ፊልሙ የተሰራጨዉ የፍርድ ቤት እግድን ጥሶ ነዉ መባሉ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ማስከበር የሚገባዉን የሐገሪቱን ሕገ-መንግሥት መጣሱን፥ የሕግ የበላይነት አለመከበሩን ያረጋግጣል የሚል ጠንካራ ትችት ገጥሞታል።ተቃዉሞ፥ ቅሬታ፥ ጥያቄዉ እና ትችቱ የሳምንቱ የዉይይት ርዕሳችን ነዉ።የሕግ ባለሙያዎችና ፖለቲከኞችን ጋብዘናል።

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic