«ኢትዮጵያ የጀመረችዉን ጉዞ ትቀጥላለች» ጠቅላይ ሚኒስትሩ | ኢትዮጵያ | DW | 07.07.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

«ኢትዮጵያ የጀመረችዉን ጉዞ ትቀጥላለች» ጠቅላይ ሚኒስትሩ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተና ዓመት የሥራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት በሚገኘዉ አዳራሽ ዉስጥ ነዉ ያካሄደዉ። በቀጥታ የም/ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ ጥያቄ በማንሳት ነዉ ጉባዔዉ የተጀመረዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:59

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ምላሽ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተና ዓመት የሥራ ዘመን 18ኛ መደበኛ ጉባዔ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት በሚገኘዉ አዳራሽ ዉስጥ ነዉ ያካሄደዉ። በቀጥታ የም/ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ ጥያቄ በማንሳት ነዉ ጉባዔዉ የተጀመረዉ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ «እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም» አሉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ የተሰበሰቡት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላነሱት ጥያቄ በሰጡት መልስና ማብራሪያ እንዳሉት ሐገርን በብሔርና በኃይማኖት እያጋጩ መንግሥት ሆኖ መቀጠል አይቻልም።ጠቅላይ ሚንስትሩ በድምፃዊ ሐጫሉ ግድያና በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሰበብ በመንግሥታቸዉ ላይ ጫና ለመፍጠር የተደረጉ ሙከራዎች እንደነበሩ መታዘባቸዉን አስታዉቀዋል።የተቃዋሚዎቻቸዉን ፖለቲካዊ መርሕም የሰከረ፣በቅናት ላይ የተመሠረተና ኢትዮጵያን የሚከፋፍል ብለዉታል።የምክር ቤቱ አባላት  ለጠቅላይ ሚንስትሩ ካቀረቧቸዉ ጥያቄዎች የጎሉት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት፣የአባይ ግድብ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዞኖች የክልልነት ጥያቄ እና ጠቅላይ ሚንስትሩ የኦሮሞ ብሔር አባል መሆን አለመሆናቸዉን የሚመለከቱ ነበሩ።ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ እንደተከታተለዉ የምክር ቤቱ አባላት በድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ  ግድያ ሰበብ ሥለተቀሰቀሰዉ ሁከት፣ግድያና የመንግሥት ርምጃ  በቀጥታ ያነሱት ጥያቄ አልነበረም።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመጪዉ 2013 ዓመት የ476 ቢሊዮን፣ 12 ሚሊዮን 952 ሺሕ ብር በጀት አፅድቋል። ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት በሚገኘዉ አዳራሽ ጉባዔ ላይ የተገኘዉን የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን ሰለምን ሙጬን ጠ/ቅላይ ሚኒስትሩ በምን በምን ጥያቄዎች ላይ ማብራርያ እንደሰጡ ጠይቀነዉ ነበር።  

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic