ኢትዮጵያ፥ የተቃዉሞ ሠልፍ ጅምር፥ ዉጤቱና ቀጣይነቱ | ኢትዮጵያ | DW | 16.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ፥ የተቃዉሞ ሠልፍ ጅምር፥ ዉጤቱና ቀጣይነቱ

የኢትዮጵያ በጣሙን የአዲስ አበባ አዉራ ጎዳኖች ከ1997 ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግሥትን የሚቃወሙ ሠልፈኞችን አደባባይ ወጥተዉባቸዋል።-አንድ ሠልፉ በሠላም ተጀምሮ በሠላም ተጠናቅቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበር ሠማዊ ፓርቲ የጠራዉ ሠላማዊ የተቃዉሞ ሠልፍ ባለፈዉ ግንቦት ሃያ-አምስት አዲስ አበባ ዉስጥ ተደርጓል።የመንግሥትን መርሕ በመቃወም አደባባይ የወጣዉ ሕዝብ ቁጥር ሥትነት እንደተመልካቹ የተለያየ ነዉ።አምስት ሺሕ፥ አስር፥ አስራ አምስት ሺሕ፥ ከዚያም በላይ የገመቱትም አሉ።

ሠልፈኛዉ ያነሳቸዉ ጥያቄዎችም ብዙ ናቸዉ። ሕገ-መንግሥቱ እንዲከበር፥ መንግሥት የሚከተለዉን ጨቋኝ መርሕ ማለትፖሊሲ እንዲቀይር፥ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፥ መንግሥት በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም፥ ሕዝብ እንዳይፈናቀል፥ ለተፈናቀሉትም ካሳ እንዲከፈል፥ የፕረስ ነፃነት፥ እንዲከበር ሌሎችንም ጥያቄዎች ተነስተዋል።ብዙዎች እንደሚሉት የጥያቄዉ ብዛት የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ እዉነት ዉስብስብ እነት አመልካች ነዉ።

የአደባባይ ሠልፉን የጠራዉ ሠማዊ ፓርቲ ሠልፈኛዉ ላቀረባቸዉ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ መንግሥት በሶስት ወር ጊዜ ዉስጥ መልስ እንዲሰጥ ቀነ-ገደብ ቆርጧል።የሠልፈኛዉ ቁጥር-ሥትነት፥ ያነሳቸዉ ጥያቄዎች ብዛት፥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስብስብነት፥ መንግሥት ለተነሱት ጥያቄዎች መልስ የመስጠቱ፥ አጠራጣሪነት፥ ይሕን መልስ የተቃዉሞ ሠልፍ የመቀጠል-አለመቀጠሉ አሁንም ወደፊትም የሚያነጋግር ነዉ።ቢያንስ ሁለት ነገር ግን ሐቅ።

የኢትዮጵያ በጣሙን የአዲስ አበባ አዉራ ጎዳኖች ከ1997 ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ መንግሥትን የሚቃወሙ ሠልፈኞችን አደባባይ ወጥተዉባቸዋል።-አንድ ሠልፉ በሠላም ተጀምሮ በሠላም ተጠናቅቋል። -ሁለት።እዉነቶቹን ይዘን የሚነጋግሩትን ጉዳዮች እየጠቃቀስን እኛም ባጭሩ እንነጋገራለን።አራት እንግዶች አሉን፥-

ነጋሽ መሐመድ

መስፍን መኮንን

Audios and videos on the topic