ኢትዮጵያ፤ የባለሥልጣናት መሻርና ምክንያቱ | ኢትዮጵያ | DW | 15.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ፤ የባለሥልጣናት መሻርና ምክንያቱ

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን ባለፈዉ መስከረም ከያዙ ወዲሕ ሚንስትሮች ከሥልጣን ሲወገዱ አቶ ሐይሉ ሁለተኛዉ ናቸዉ።።አቶ መላኩን ጨምሮ ባንድ ጊዜ በርካታ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሥልጣን ሲወገዱ ወይም ሲከሰሱ ደግሞ የሰሞኑ የመጀመሪያዉ ነዉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ የሐገሪቱን የፍትሕ ሚንስትር፥ የገቢዎችና የጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ሐላፊ፥ ምክትላቸዉንና ሌሎች ባለሥልጣናትን ከየሥልጣናቸዉ አስወግዷል። መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት የፍትሕ ሚንስትር አቶ ብርሐን ሐይሉ ከሥልጣን የተነሱት አቅም አንሷቸዋል በሚል ምክንያት ሲሆን፥ የጉምሩክ ሐላፊ አቶ መላኩ ፈንታ እና የበታቾቻቸዉ ደግሞ በሙስና ተዘፍቀዋል በሚል ነዉ።አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን ባለፈዉ መስከረም ከያዙ ወዲሕ ሚንስትሮች ከሥልጣን ሲወገዱ አቶ ሐይሉ ሁለተኛዉ ናቸዉ።ከዚሕ ቀደም የአቅም ግንባታ ሚንስትር የነበሩት አቶ ጁኔዲን ሳዶ ከስልጣን ተወግደዋል።አቶ መላኩን ጨምሮ ባንድ ጊዜ በርካታ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሥልጣን ሲወገዱ ወይም ሲከሰሱ ደግሞ የሰሞኑ የመጀመሪያዉ ነዉ።አልበዛም ወይ? ምክንያቱስ  በርግጥ የአቅም እጦት፥ ሙስና፥ ዋልጌነት ወይስ ሌላ፥-የምሥራቅ አፍሪቃና የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉዳይ ፖለቲካ ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲንን በስልክ ጠይቄያቸዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች