ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
መድረኩ ዓለም አቀፋዊ በተለያዩ ቋንቋዎች በአንድ ርዕስ ስር የሥነ-ጽሑፍ እና የሥነ-ግጥም ክህሎት የሚታይበት ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ መድረኩ ከአስር የተለያዩ ሃገራት የመጡ የኪነ-ጥበብ ሰዎች የሚሳተፉበት ነዉ። በዚህ ዓመት መድረኩን ያዘጋጀሁት እኔ ነኝ ። የዚህ ዓመት ርዕሳችን የድምፅ መረጃዎችን በማህደር ማስቀመጥ ይላል።
ላለፉት ቀናት በሀረር ሲካሄድ የቆየው 1443 ኛው የሸዋል ኢድ በዓል ደማቅ እና አስደሳች መሆኑን የሀገር ውስጥ እና ከውጭ በበዓሉ የታደሙ አስተያየት ሰጭዎች ገለፁ። በዓሉ የሀረርን ቅርሶች ለማስተዋወቅ እና በተለያየ ምክንያት ተቀዛቅዞ ለቆየው ቱሪዝም መነቃቃት መፍጠሩን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል።
በሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምበላላ ከታደሙት መካከል አብዛኞቹ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ በተለይ በዓሉን በጋራ በሚያከብሩትና ጉዱማሌ በተባለው የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ላይ የብሄሩ ወንዶችና ልጃገረዶች በባህላዊ አልባሳቶች አጊጠው የበዓል ጭፈራዎችን አከናውነዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘዉ የሲምሶንያን ኢንስቲትውት የተፈጥሮ ሳይንስ ሙዝየም ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ዮሐንስ ዘለቀም በጥናቱ ተሳትተፈዋል። በዚህ በያዝነው ዓመት በታኅሣሥ ወር ቡድኑ ባካሄደው ጥናት ከፍተኛ የሆነ የእንስሳት ቅሪተ አካል እና የጥንት ሰዎች የተገለገሉባቸው የድንጋይ መሣሪያ ክምችቶች አግኝተዋል፡፡