ኢትዮጵያ የሚኖሩ ወጣቶችና የዕረፍት ቀናት | ባህል | DW | 27.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ኢትዮጵያ የሚኖሩ ወጣቶችና የዕረፍት ቀናት

የትምህርት ቤት ዕረፍት ቀናት ሲመጣ ወጣቱ ጊዜውን በምን ያሳልፋል? ይህ እንደ ቦታው እና እንደ አቅም ሁኔታ ይለያያል። ከዚህ ቀደም በዋሽንግተን ዲሲ የቅዳሜ ምሽታቸውን አንድ ስዕል መሳል ወደ የሚቻልበት ማዕከል በመሄድ ትርፍ ጊዜአቸዉን የሚያሳልፉ ወጣቶችን አነጋግረን ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:16
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
09:16 ደቂቃ

የዕረፍት ቀናት

ሳምንቱ እስኪገባደድ እና የትምህርት ቤት ዕረፍት ጊዜ እስኪደርስ የሚጠብቁ በርካታ ወጣቶች አሉ። ለምሳሌ በዚህ በጀርመን ትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ወጣቶች ቅዳሜ እና እሁድን ፤ በዋና፣ ሲኒማ እና ቲያትር ቤት በመግባት፣ ሙዚቃ ወዳለበት ጭፈራ ቤት በመሄድ ዓይነት ነገሮች ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። ከዚህ ውጪ የጀርመን ወጣቶች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት ድረ-ገፅ ኦንላይን በመግባት እንደ ፌስቡክ እና ዮ ቱይብ ገፆችን በመጎብኘት ነዉ። ኢትዮጵያ የሚኖሩት ወጣቶች የዕረፍት ቀናታቸውን እንዴት እንደሚያሳልፉ ከድምፅ ዘገባው ማዳመጥ ይችላሉ።

ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic