ኢትዮጵያ እንደና ተራበች፦ እንደግና ለምን | ኢትዮጵያ | DW | 02.11.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እንደና ተራበች፦ እንደግና ለምን

በሌሎች መስኮች ያለዉ ችግር በተለይም የፖለቲካዉ አለመረጋጋት ከኢኮኖሚዉ ፓሊስ ግራ አጋቢነት በላይ የረሐብ ዑደቱ እንዳይሰበር ትልቅ እንቅፋት ነዉ።

default

02 11 09 ኢትዮጵያ የሁለት አሐዝ የምጣኔ ሐብት እድገት ማስመዝገቧ እየተነገረባት፦ የረሐብተኞችን ሕይወት ለማዳን እንደገና የሚለመንባት-የሚለመንላት ሐገር ሆናለች።አመት ዞሮ በገጠመ ቁጥር የረሐብ ዑደት የመቀጠሉ ሠበብ-ምክንያትም እንደገና ያነጋግር ያከራክር ይዟል።ንግግር-ክርክሩ የዛሬ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።በቦን ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚ መምሕርና ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሰዒድ ኑሩን ለምንና እንዴት ብለናቸዋል።ላፍታ አብራችሁን ቆዩ። ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------ ለምን እንራባለን?ዉሐና ዝናብ ሥለጠፋ? ሥንፍና ወይስ የመንግሥት መርሕ? ለዶክተር ሰኢድ ሰወስተኛዉ ዋና ምክንያት ነዉ። ድምፅ እንደ ኢትዮጵያ አብዛኛ ሕዝባቸዉ በግብርና የሚተዳደርባቸዉ፥ የእርሻ ግብአት እጥረት ባለባቸዉ፥ ዘመናይ አስተራረስ ባልዳበረባቸዉ ሐገራት የመሬት ፖሊሲ ወይም መርሕ አስቸጋሪ እና ዉስብስብ ነዉ-ኢኮኖሚስቱ እንደሚሉት።እሁለት በሚቦደኑ ብዙ ምክንያቶች።መሬትን መንግሥት ሲቆጣጠረዉና መሬት ለግል ባለሐብት ሲዞር፥-የመጀሪያዉ፣- መንግሥት መሬትን ሲቆጣጠረዉ ድርቅ መጣ ረሐብ ገባ ነዉ-ዉጤቱ እንደ ዶክተር ሰዒድ። ድምፅ ነበር! ግን አልተደረገም።ረሐብን መከላከሉም አልተቻለም።ምናልባት መንግሥት ረሐብን እንደ ብሔራዊ ክብር ዉርደት አይቶት-የቀድሞዉ መንግሥት ይዟቸዉ የነበሩ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እንደያዘ ቢቀጥል ኖሮ ወይም ከግል ባለሐብቶች ጋር ቢሰራባቸዉ ኖሩ፥ ያልተቻለዉ ግን ይቻል የነበረዉ ይቻል ይሆን ነበር። ድምፅ ይሕም አልተደረገም።የረሐብ ዑደትም ቀጥሏል።በቅርቡ ለእርሻ የሚዉሉ ሠፋፊ መሬቶችን መንግሥት ለዉጪ ባለሐብቶች መስጠቱ መሬትን መንግሥት መቆጣጠር የለበትም ለሚለዉ ትችት ገሚስ መልስ ይመስል ይሆናል።እርምጃዉ ግን ከማከራከር አልፎ-እያወዛገበ ነዉ።ለምን?-አስቸጋሪ ይሉታል ዶክተር ሰኢድ ጥያቄዉን። ድምፅ የዚሕም መርሕ ወይም ፖሊሲ ግልፅ አይደለም።እና ረሐብን ለመከላከል ለወደፊቱም ቢሆን መፈየዱ አጠራጣሪ ነዉ።ከመርሆቹ ባለፍ የአፈፃቸማቸዉ ግራነት ደግሞ ዉጤቱን ግራ አድርጎታል።በሌሎች መስኮች ያለዉ ችግር በተለይም የፖለቲካዉ አለመረጋጋት ከኢኮኖሚዉ ፓሊስ ግራ አጋቢነት በላይ የረሐብ ዑደቱ እንዳይሰበር ትልቅ እንቅፋት ነዉ። ድምፅ ሌላ አመት፥ ሌላ ትርምስ ሌላ ረሐብ።ኢትዮጵያ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ከምኞች ሌላ ምን-ይባላል።ቸር ያሰማን።

Audios and videos on the topic