ኢትዮጵያ እና ግብፅን ያፋጠጠው አባይ ወንዝ | አፍሪቃ | DW | 21.09.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ኢትዮጵያ እና ግብፅን ያፋጠጠው አባይ ወንዝ

ርዝመቱ 6650 ኪሎ ሜትር ይጠጋል። የተጠቃሚዎቹ ሕዝብ ቁጥር አንድ ላይ ቢደመር ወደ አምስት መቶ ሚሊዮን ይደርሳል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:04

አባይ አሁንም ማነታረኩን እንደቀጠለ ነው

ርዝመቱ 6650 ኪሎ ሜትር ይጠጋል። የተጠቃሚዎቹ ሕዝብ ቁጥር አንድ ላይ ቢደመር ወደ አምስት መቶ ሚሊዮን ይደርሳል፤ የአባይ (ናይል) ወንዝ። ኢትዮጵያ እና ግብፅን በዲፕሎማሲው መስክ በተደጋጋሚ በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲገናኙ እና እንዲነጋገሩ አድርጓል። ከሰሞኑ ግን ግብፅ ይዛ የቀረበችው ሐሳብ ለኢትዮጵያ የሚዋጥ አይመስልም። ግብፅ የህዳሴው ግድብ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውኃ በየዓመቱ ይልቀቅ በሚል ያቀረበችው ሐሳብ በኢትዮጵያ የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂኒየር ስለሺ በቀለ በኩል የማይሆን ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው። የናይል ወንዝ ለኢትዮጵያ፤ ግብጽ እና ሱዳን የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ እንደኾነ በበርካታ ታዛቢዎች ይነገራል። ሦስቱ ሃገራት ሰሞኑን ተገናኝተው ኢትዮጵያ በምትገነባው የህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል ላይ ከስምምነት ሳይደረስ ተለያይተዋል።  

ይልማ ኃይለሚካኤል

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic