ኢትዮጵያ እና የዲያስፖራው ተሳትፎ | ኢትዮጵያ | DW | 31.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እና የዲያስፖራው ተሳትፎ

በግምት ወደ ሁለት ሚልዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ምክንያቶች በውጭ አገሮች እንደሚኖሩ የፍልሰት ፖሊሲ ጥናት ተቋም ያወጣቸው መዘርዝሮች ያሳያሉ። እነዚሁ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሀገር ልማት ላይ ለማሳተፍ መንግሥት ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የማበረታቻ እቅድ አውጥቶ እየሰራ ይገኛል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 30:50

የዲያስፖራው ተሳትፎ

በዚሁ ማበረታቻ በመሳብ አንዳንዶች በውጭ ያካበቱትን ዕውቀት፣ የስራ ልምድ፣ ክሂሎት እና መዋዕለ ንዋይ ይዘው ወደአገር በመመለስ በሚፈልጉባቸው የስራ መስኮች በመሰራት፣ በአገር ውስጥ ካሉት ስራ ፈጣሪዎች ጎን ድርሻ እያበረከቱ መሆናቸው ይነገራል። ከተመላሾች እንደምንሰማው ከብዙ ዓመት የውጭ ሀገር ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ተመልሶ የመስራቱ ሂደት ብዙ ውጣ ውረድ አአለው። አዳጋችም ሊሆን ይችላል። በዛሬው የውይይት ክፍለ ጊዜ ተመላሾቹ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓላማቸውን እግብ ለማድረስ የሚያደርጉትን ጥረት ይመለከታል።

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች