ኢትዮጵያ እና የአዉሮጳ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዘገባ | ኢትዮጵያ | DW | 09.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እና የአዉሮጳ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዘገባ

የ ግንቦት 2002 ዓ ም የኢትዮጵያን ምርጫ የታዘበው የአውሮጳ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ዋናውን ዘገባውን ትናንት በብራስል አወጣ።

default

ታይስ በርማን

ባለፈው ነሀሴ መውጣት የነበረበት ዘገባ በአዲስ አበባ ላልወጣበት ድርጊት ምክንያቱ የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ በመከልከሉ መሆኑን የቡድኑ መሪ እና የአውሮጳ ፓርላም እንደራሴ ታይስ ቤርማን ገልጸዋል። ሚስተር ቤርማን በዘገባቸው የኢትዮጵያ መንግስት በህዝብ ሀብት በመጠቀም የፖለቲካ ምህዳሩን ለፖለቲካ ፓርቲዎች በማጥበቡ ምክንያት ትክክለኛ እና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫ ለማካሄድ አለመቻሉን አመልክተዋል። የምርጫው ታዛቢ ቡድን ለፍትሃዊና ለዴሞክራሲያዊ ግንባታ ወደፊት ሊደረጉ ይገባቸዋል ያላቸውን ሀሳቦች በዘገባው አስቀምጦዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic