ኢትዮጵያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ | ኢትዮጵያ | DW | 31.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄ

አምስት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ዓለም ዓቀፍ መርማሪ ቡድን ኢትዮጵያ እንዲገባ እንዲፈቅድ ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ ጠየቁ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:06

ኢትዮጵያ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥያቄየኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ይወስዳል የሚባለውን የኃይል እርምጃ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያጣራ ዓለም ዓቀፍ መርማሪ ቡድን ወደ ሃገሪቱ እንዲገባ እንዲፈቅድ በድጋሚ ተጠይቋል ። ጥያቄው የቀረበው አምስት የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ትናንት ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው ። ጥያቄውን በጋራ ያቀረቡት ድርጅቶች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፣ «DEFEND DEFENDERS» የተባለው ለሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ደህንነት የቆመው ድርጅት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ማኅበር ፣ግንባር ቀደም የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ «FRONTLINE DEFENDERS» እና ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ፌደሬሽን የተባሉ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ናቸው። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic