ኢትዮጵያ እና የሁለቱ ሱዳኖች ሽምግልና | አፍሪቃ | DW | 03.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኢትዮጵያ እና የሁለቱ ሱዳኖች ሽምግልና

ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ እንዲነጋገሩ የጋበዙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ና የአፍሪቃ ህብረት መሪዎቹ በመስከረም የደረሱበት ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ነገ አዲስ አበባ ውስጥ የሚካሄደው የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ውይይት የተሳካ ውጤት ያስገኛል ብላ ተስፋ እንደምታደርግ ኢትዮጵያ አስታወቀች ። ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ ውስጥ እንዲነጋገሩ የጋበዘችው ኢትዮጵያ የተጋታው የሱዳን የሠላም ጥረት ወደፊት ይራመዳል የሚል አዎንታዊ አስተያየት እንዳላት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ሁለቱ መሪዎች አዲስ አበባ እንዲነጋገሩ የጋበዙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ና የአፍሪቃ ህብረት መሪዎቹ በመስከረም የደረሱበት ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በሠላሙ ጥረት የኢትዮጵያን ሚናና ከውይይቱ ስለሚጠበቀው አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በስልክ አነጋግረናችዋል ።

ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች