ኢትዮጵያ እና ምርጫ 2007 | ኢትዮጵያ | DW | 24.05.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እና ምርጫ 2007

ከማለዳ ጀምሮ በመላ አገሪቱ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 5ኛው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በነፃነት ለሚፈልገው ፓርቲም ሆነ ዕጩ ድምፁን በመስጠት ላይ ይገኛል ሲል የሃገሪቱ መገኛኛ ብዙኃን ዘገቡ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስታወቀዉ መሠረት ዛሬ ዕሁድ የሚደረገዉን ምርጫ አጠቃላይ ዉጤት ይፋ ለማድረግ ከድምፅ መስጪያዉ ዕለት በኋላ አንድ ወር ያሕል ጊዜ ይወስዳል።

ይሁንና የምርጫ ጣቢያዎች የየአካባቢያቸዉን ምርጫ ዉጤት በየአካባቢያቸዉ ማሳወቅ እንደሚችሉ ተመልክቶአል። በአዲስ አበባ በሆሳዕና እና በአምቦ የሚገኙ ዘጋቢዎቻችን የተመለከቱዋቸዉን በፎቶና በድምፅ እየዘገቡ ናቸዉ።

ዶቸ ቬለ የአማርኛ አገልግሎት የድምፅ አሰጣጡን ሒደት በቀጥታ ይከታተላል።እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚገኙ ዘጋቢዎቻችን፤ ከዚሕ ከቦንና ከሌሎችም አካባቢዎች የምናጠናቅራቸዉን ዘገቦች ከራዲዮ ሥርጭታችን በተጨማሪ በድረ ገጻችንwww.dw.de/amharic ላይ (Live-Blog)መከታተል ትችላላችሁ። በፌስ ቡክ ገፃችንም ሥለምርጫዉና ከምርጫዉ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በሚመለከት ከድምፅ መስጫዉ ዕለት ጧት ጀምራችሁ እስኪጠናቀቅ ድረስ እርስ በርስና ከኛ ጋር ተወያዩ።

በድምፅ መስጪያዉ ዕለት ያነሳችሁትን ፎቶ ግራፍ፤ በፌስ ቡክ ገፃችን፤ ትዝብታችሁን ደግሞ SMS ላኩልን።የSMS መቀበያ ቁጥራችን 0049 172 26 66 944 ነዉ።ሥልክ መደወል ከቻላችሁም 0049 228 429 164 995 መልዕክት ብትተዉሉን ይደርሰናል።እናሰራጨዋለንም።የድምፅ አሰጣጡ ሒደት «ተዛብቷል» ብላችሁ ካመነችሁ አስተያየታችሁን ብትልኩልን የሚመለከተዉን ወገን አነጋግረን መልስ ለማግኘት እንሞክራለን። መልካም ምርጫ።

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ