ኢትዮጵያ እስረኞች መፍታቷን ትቀጥል-ሜርክል | ኢትዮጵያ | DW | 12.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ እስረኞች መፍታቷን ትቀጥል-ሜርክል

መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ኢትዮጵያ እስረኞች የመልቀቅ እርምጃዋን እንድትቀጥል ጠየቁ። መራሒተ-መንግሥቷ ዛሬ ከጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጀርመን መንግሥት ቃለ አቀባይ ሽቴፈን ዛይበርት ገልጸዋል። 

መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ኢትዮጵያ እስረኞች የመልቀቅ እርምጃዋን እንድትቀጥል ጠየቁ። መራሒተ-መንግሥቷ ዛሬ ከጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የጀርመን መንግሥት ቃለ አቀባይ ሽቴፈን ዛይበርት ገልጸዋል። 

ሁለቱ መሪዎች በዛሬው የስልክ ውይይታቸው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ መወያየታቸውን ቃል-አቀባዩ ተናግረዋል ። የጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም መንግሥት ከወትሮው በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው እስረኞች መልቀቁን ያደነቁት መራሒተ-መንግሥቷ እርምጃውን "መልካም ነው" ሲሉ ጠርተውታል። መንግሥት እስረኞችን መልቀቁን እንዲቀጥል ሜርክል ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ፖለቲከኛ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 746 እስረኞች ለመፍታት መወሰኑን አስታውቆ ነበር። የፌድራል ጠቅላይ አቃቤ-ሕግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሰባት የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ አመራሮች እና አባላት ክስ እንዲቋረጥ መወሰኑን ገልጿል። የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ካስተላለፈው ውሳኔ በኋላ በመጀመሪያው ዙር ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ 528 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተለቀዋል። 

መራሒተ-መንግሥት ሜርክል ከጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምኅዳር ለማስፋት ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አበረታተዋቸዋል።

ላለፉት 27 አመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ምኅዳሩን እንዲያሰፋ ከተለያዩ ወገኖች ጫና እየበረታበት መምጣቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ።  

እሸቴ በቀለ

ተስፋለም ወልደየስ 

 

ተዛማጅ ዘገባዎች