ኢትዮጵያ በውጭ የሚገኙ ዜጎች በባንክ ሥራ እንዲሰማሩ የመፍቀዷ ፋይዳ | ኤኮኖሚ | DW | 06.08.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኤኮኖሚ

ኢትዮጵያ በውጭ የሚገኙ ዜጎች በባንክ ሥራ እንዲሰማሩ የመፍቀዷ ፋይዳ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በባንክ ሥራ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ አዋጅ አፅድቋል። በምክር ቤቱ የ የገቢዎች፣ የበጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ለምለም ሐድጎ አዲሱ አዋጅ በአገሪቱ ምጣኔ-ሐብታዊ ዕድገት እንዲሳተፉ ያግዛል ሲሉ ጠቀሜታውን አስረድተዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17

የባንክ ሥራ አዋጅ መሻሻል ፋይዳ

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የተሻሻለው የባንክ አሰራር ህግ የውጭ ምንዛሪ ግኝትንና ከውጭ የሚገኝ የፋይናንስ ሃብትን የሚያሳድግ ውሳኔውም ተገቢ ግን የዘገየ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያ ተናገሩ።
የህግ ማሻሻያ ጥያቄው በሁሉም የአለም አቅጣጫ ካሉ ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊያን በየጊዜው ሲነሳ የነበር መሆኑም በሃገሪቱ የባንክ ልማት ዘርፍ ጉልህ በጎ ተጽእኖ የሚኖረው ነው ተብሏል።
ነባሩ ህግ ኢትዮጵያዊያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ከዚህ ስራ አርቆ የቆየ በመሆኑ የፋይናንስ ሴክተሩ ተወዳዳሪና ጠንካራ እንዳይሆን አድርጎት መቆየቱን በኮተቤ ሜትሮ ፖሊታን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶክተር መኮንን ካሳሁን ተናግረዋል።
ዳያስፖራው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሸር የመግዛት ፣ ባለቤት የመሆንና ባንክ የመቋቋም መብቱ በህግ መፈቀዱ የረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄው መመለሱን ያረጋገጠበት እና ዝርዝር አሰራሩ ልማት ባንክ በሚያወጣቸው መመርያዎች ይታያል ያሉት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ህጉ መሻሻሉን እና እድሉ መከፈቱን ተከትሎ ሊከሰት የሚችልን የጎንዮሽ ጉዳት ለመከላከልም መንግስት ክትትል
ያደርጋል ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic