ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ | ስፖርት | DW | 11.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ኢትዮጵያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን፣ በመጪው ሰኔ ወር በብራዚል ለሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አፍሪቃን ወክለው ከሚገኙት 5 ቡድኖች አንዱ ሆኖ ለማለፍ ፣ከናይጀሪያ ጋር የቀሩት 2 የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ናቸው።

የመጀመሪያው ዙር፣ ከነገ በስቲያ አዲስ አበባ ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን፤ ሁለተኛውና የመጨረሻው ግጥሚያ አቡጃ ላይ ቅዳሜ ኅዳር 7 ቀን 2006 ይሆናል የሚካሄደው። ከሁለቱ ቡድኖች በአጠቃላይ ውጤት አሸናፊ የሚሆነው ስለሚያልፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በራሱ ሜዳ አስተማኝ ነጥብ ለማግኘት ጠንክሮ መጫዎት ይጠበቅበታል።

ከነገ በስቲያ እሁድ፣ አዲስ አበባ ላይ ለሚካሄደው ወሳኝ ግጥሚያ
የኢትዮጵያ ቡድን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለጃፈር ዓሊ የገለጹት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው፣ አንድ ኣጥቂ ብቻ በጉዳት ምክኒያት መሰለፍ አለመቻሉን አረጋግጠዋል።

ለቡድኑ ፤ አንዱ ጥንካሬ ሰጪ ፣ የኳስ አፍቃሪዎች ድጋፍ መሆኑ አያጠራጥርም። ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የህዝብ አስተያየት አሰባስቦ ልኮልናል።

ጃፈር ዓሊ

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic