ኢትዮጵያውያን እስረኞች በየመን | ኢትዮጵያ | DW | 13.02.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያን እስረኞች በየመን

በየመን እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እስረኞች የፍትህ ያለህ እያሉ ነው። ከ 15 ዓመታት በላይ በየመን እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ እንደሚገኙ የገለጹት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ያለኣንዳች ማስረጃ ከ 25 ዓመት እስከ ይሙት በቃ ተፈርዶብናል ባይ ናቸው።

በዚያች ኣገር ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አቤቶታ ብናቀርብም ሰሚ ኣላገኘንም ሲሉም ኣማሯል። የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ኢምባሲዎች የዜጎችን መብት የማስከበር ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሶ ችግሮቹን በቀጥታ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ማቅረብም እንደሚቻል ጠቁመዋል።

በሶማሊያ በኩል ኣድርገው በጀልባ ባህር ኣቐርጠው ወደ የመን እንደገቡ የሚናገሩት እነዚህ ኢትዮጵያውያን እስረኞች ያኔ ተይዘው ሲታሰሩ 11 ነበሩ። ኣሁን ያሉት 9 ሲሆኑ ሁለቱ እነሱ እንደሚሉት እዚያው ሸቡዋ በሚባል እስር ቤት ውስጥ ሞቷል። በጥይት ቆስሎ በቂ ህክምና ሳያገኝ የሚሰቃይ እና የዓዕምሮ ህመምተኛ የሆነም ኣለ። ከታሰሩ ድፍን አስራ አምስት ዓመታትን ኣስቆጥረናል የሚሉት እነዚሁ እዝረኞች የፖለቲካ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ ስደተኛ እንደሆኑ ነው የሚናገሩት። ያለኣንዳች ማስረጃ ከ 25 ዓመት እስከ ሞት እንደተፈረደባቸው እና ከምግብ ጀምሮ በእርዛት እና ህክምና በማጣት እየተሰቃዩ መሆናቸውንም በምሬት ገልጿል።

ከየመን መንግስት በኩል ፍትህ ማጣታቸው ሳያንሳቸው በዚያች ኣገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲም ችግሩን እያወቀ ሊረዳን ኣልቻለም ኣሊያም ኣልፈለገም ሲሉም ኣማሯል። የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ቃ/ኣቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ኢምባሲዎች የዜጎችን መብት የማስከበር ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰው በመረጃ ውስንነት ሰዎች ሊጎዱ እንደሚችሉ ግን ኣልሸሸጉም። ስደተኞች ችግር ከደረሰ በኃላ ብቻ ሳይሆን ችግር ከመድረሱ በፊትም የሚገኙበትን ሁኔታ ለኢምባሲ መረጃ ቢሰጡ የተሻለ እንደሚሆን የጠቀሱት ቃል ኣቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ስደተኞች ለኢምባሲ ኣመልክተው ምናልባት በዚያ በኩል ዕልባት ካላገኙም እንኩዋን በቀጥታ ለውጪ ጉዳይ ሚ/ር ቢያሳውቁ መፍትሄ መሻት እንደሚቻም ጠቁመዋል።

ጃፈር ዓሊ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic