ኢትዮጵያውያን ተመላሾችና የጀርመን እገዛ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ኢትዮጵያውያን ተመላሾችና የጀርመን እገዛ

ዶክተር ኤፍሬምና የምሥራች እንደሚሉት የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል በጀርመን እውቀትና የሥራ ልምድ ያካበቱ ምሁራን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሚፈለጉባቸው የሥራ መስኮች እንዲያገለግሉ የሚሰጠው ድጋፍ ጠቀሜታ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም ።

ከጀርመን ወደ ኢትዮጵያ በፍላጎታቸው ለሚመለሱ ኢትጵያውያን ምሁራን እገዛ ከሚያደርገው የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል ድጋፍ ያገኙ ተመላሾች ተመክሮ የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

ዶክተር ኤፍሬም ገብረ ማርያምና ና የምሥራች ነጋሽ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ጀርመን የተከታተሉ በአሁኑ ሰአት ደግሞ በሰለጠኑበት ሞያ ኢትዮጵያ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ምሁራን ናቸው ። ዶክተር ኤፍሬም ከበርሊኑ ፍሪ ዩኒቨርስቲ በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል ። ያጠኑት መልክአ ምድርን የተመለከቱ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ማቀነባበርና በተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም ና በመሳሰሉት  ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ ነው ።  የዛሬ 2 አመት ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ ወዲህ በሰጠኑበት መስክ አገልግሎት በሚሰጠው «ESystems አፍሪቃ »በተባለ የግል ድርጅት ውስጥ ይሰራሉ ። በዩኒቨርስቲም ያስተምራሉ ። ዶክተር ኤፍሬም ወደ ኢትዮጵያ በፍላጎታቸው ለሚመለሱ ኢትጵያውያን ሥራ በመፈለግና ገንዘብ በመደጎም ከሚረዳው የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል እገዛ ከሚያገኙ ተመላሾች አንዱ ናቸው ። ዶክተር ኤፍሬም እንደሚሉት ግን ወደሃገራቸው የተመለሱት ይህ መርሃ ግብር በመኖሩ ብቻ አይደለም ።

የምሥራች ነጋሽ በጀርመኑ የካስል ዩኒቨርስቲ 2ተኛ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ትምህርት ጥናትና ምርምር አጠናቀው ባለፈው አመት በሚያዚያ ነበር ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ።    በኢትዮጵያ አርክቴክቸር ህንፃ ግንባታና የከተማ ልማት ተቋም ውስጥ በሰለጠኑበት ሞያ እየሰሩ ነው ። እርሳቸውም እንደ ዶክተር ኤፍሬም ከጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል መርሃ ግብር ተጠቃሚ ናቸው ።

ዶክተር ኤፍሬምና የምሥራች እንደሚሉት የጀርመን አለም አቀፍ የፍልሰትና የልማት ማዕከል በጀርመን እውቀትና የሥራ ልምድ ያካበቱ ምሁራን ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በሚፈለጉባቸው የሥራ መስኮች እንዲያገለግሉ  የሚሰጠው ድጋፍ ጠቀሜታ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም ። የምሥራች

ዶክተር ኤፍሬም መርሃ ግብሩ በተለይም ባለሞያዎች ከተማሩባቸው መስኮች ውጭ የተሻለ ጥቅም ሊያገኙባቸው ወደ ሚችሉ ሥራዎች እንዳያተኩሩ ከፍተና እገዛ ያደርጋል ይላሉ ።

ሁለቱም ተመላሾች በበኩላቸው ማዕከሉ የሚሰጠው አገልግሎት እምብዛም የሚተች አይደለም ይላሉ ። ሆኖም ቢሻሻሉ ያሏቸው አሰራሮች አልጠፉም ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic