ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ | ኢትዮጵያ | DW | 12.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ

በዋሽንግተን ዲሲ አከባቢ የሚንቀሳቀሰው የወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ማህበር የተባለ ስብስብ ባለፈው ቅዳሜ በቨርጂንያ ግዛት አሌክሳንድርያ ከተማ አምስተኛ የምስረታ ዓመት በአሉን አክብሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:00 ደቂቃ

ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ማህበር

ማህበሩ ለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሥራ እድል የሚፈጠርበትን የግንኙነት መስመር የማመቻቸት ሥራ ይሠራል። በተለያዩ መሥረያ ቤቶች የሚያገለግሉ ኢትዮጵያውያን ለሌሎች ሥራ ፈላጊዎች ስልጠናና ምክር የሚሰጡበትን መድረክም ያመቻቻል። የማህበሩ መሪዎች እንደሚሉት በኮሌጆችና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲበረቱም ያግዛል ማህበሩ። አጫጭር ስልጠና ወስደው ገቢያቸውን ለማሻሻል ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንም የተመቻቹ እድሎች አሉ እንደ ማህበሩ መሪዎች ገለጻ።

በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ዘጋቢያችን የወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ማህበር እንቅስቃሴን በተመለከተ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic