ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በደቡብ አፍሪቃ | አፍሪቃ | DW | 14.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በደቡብ አፍሪቃ

በደቡብ አፍሪቃ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በፖሊሶች እንደሚሳደዱ እና እንደሚዘረፉ ዛሬ ለዶቼቨለ አማርኛው ክፍል ገለፁ። የደቡብ አፍሪቃ ፖሊሶች በፈረሶች ላይ ሆነው በውሾች ጭምር በመታገዝ እያሳደዱ እንደሚይዟቸውና ገንዘብ እንደሚወስዱባቸው ስደተኞቹ ተናግረዋል።

በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር አቶ ታምሩ አበበ እንደገለፁት ከሆነ ችግሩ መከሰቱን እንደሰሙ ወደ ቦታው ሶስት የማኅበረሰቡ ተወካዮችን ቢልኩም ፖሊሶች ተወካዮቹን ሰላዮች ናችሁ በሚል እስረዋቸዋል። ይህን የኢትዮጵያውያን ስደተኞቹን ችግር በተመለከተ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ደቡብ አፍሪቃ ደውዬ ኢትዮጵያውያኑን አነጋግሬያለሁ። ካነጋገርኩዋቸው መካከል ሊምፖፖ አውራጃ ቴፍሎፕ የሚባል አካባቢ ነዋሪ በሆኑት አቶ ዳንኤል አባቾ እንጀምራለን።


ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic