1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያንን የሚፈታተነው የዋጋ ግሽበት

ሐና ደምሴ
እሑድ፣ ጥቅምት 10 2017

የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በጥቅምት ወር ተግባራዊ እንደሚሆን የገንዘብ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ጭማሪው ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ግሽበት ኢትዮጵያውያንን በሚፈትንበት ወቅት ነው። በወር 8 ሺሕ ብር የሚከፈላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ 3 ሺሕ ብር የቤት ኪራይ ከፍለው፤ አስቤዛ ሸምተው ወጪያቸውን ለመሸፈን እንደሚጨነቁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4m0Fa
የኢትዮጵያ ብር
ለኢትዮጵያ መንግሥት ሠራተኞች የታቀደው የደመወዝ ጭማሪ በጥቅምት ወር ተግባራዊ እንደሚሆን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። ምስል MICHELE SPATARI/AFP

ኢትዮጵያውያንን የሚፈታተነው የዋጋ ግሽበት

በኢትዮጵያ እያሻቀበ የመጣው የዋጋ መናር ማቆሚያ አላገኘም። አዲሱ አመት 2017 መግባቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አግልግሎት፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የውሀ እና ፍሳሽ ሁሉም የታሪፍ ማሻሻያው  መድረጋቸውን አሳውቀዋል።

የፍራንኮ ቫሉታ መፈቀድ ጥቅሙና የጎንዮሽ ጉዳቱ

በያዝነው ወር የተደረገው ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ማህበረሰቡን ክፍኛ አስጨንቆታል። ይህንን የነዳጅ ዋጋ ጭመሪ ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች በሚሰጡት አገልግሎት ላይ   አዲስ ታሪፍ ተግባራዊ አድርጎዋል።

 "የዋጋ ግሽበቱ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይላል"

ወቅታዊውን  የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች  ወጪዎችን ከግምት ውስጥ አስገብቶ የተሰራ  ነው የተባለው   የታሪፍ  ማሻሻያ ጭማሪ በከተማዋ  ለትራንስፖርት የሚደርግ  ወጭን በእጥፍ እንዲጨምር አድርጎታል ፣ ይህ ብቻ ሳይሆን   ለሌሎች አገልግሎቶች እንደ መንጃ ፍቃድ እና ፓስፖርት ለማውጣትም ሆነ ለማደስ  የሚከፈለው ገንዘብ  እስከ መቶ ፐርሰንት ጨምሮዋል። 

የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?

ይህ የዋጋ ጭማሪ   በነዋሪዎች ላይ ያሳደረባቸውን ጫና  ለዶቼቪሌ የተናገሩት ግለሰቦች  ኑሯችን በአስማት ነው ሲሉ  ደመወዛቸው ወጫቸው መሽፈን እንዳልቻለ ይናገራሉ የመዲናይቱ ነዋሪ እንዲህ በኑሮ ጭና እየተማረረ እና የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ለከፍተኛ ትራንስፖርት ወጪ   ለምግብ እና ለቁሳቁስ ዋጋ  መናር  አይነተኛ ምክንያት መሆኑ እየታወቀ   መንግስት የተደረገው  የዋጋ ማሻሻያ ውሳኔው አስፍላጊ ነው ሲል ተናግርዋል።

ሐና ደምሴ 
እሸቴ በቀለ