ኢትዮጵያውያኑ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፋራህ ይገጥማሉ | ስፖርት | DW | 12.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ኢትዮጵያውያኑ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከፋራህ ይገጥማሉ

ኤርትራውያኑ አሮን ክፍሌ እና አወል ሐብቴ አገራቸውን ወክለው በውድድሩ ይካፈላሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:26
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:26 ደቂቃ

ኢትዮጵያውያኑ በለንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሞ ፋራህ ይገጥማሉ

ዛሬ ምሽት ኢትዮጵያውያኑ ሙክታር ኢድሪስ፤ዮሚፍ ቀጀልቻ እና ሰለሞን ባረጋ በለንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5,000 ሜትር ከሞ ፋራህ ጋር ይገጥማሉ። ከመም ውድድር በዛሬው ምሽት የሚሰናበተው ሞ ፋራህ በ17 አመቱ ሰለሞን ባረጋ ሊፈተን ይችላል ተብሏል። 
ኤርትራውያኑ አሮን ክፍሌ እና አወል ሐብቴ አገራቸውን ወክለው በውድድሩ ይካፈላሉ። ሲሩስ ሩቶ ብቸኛው ኬንያዊ ነው። ውድድሩ ምሽት 4:20 ላይ ይከናወናል፡፡ በለንደኑ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10,000 ሜትር ያሸነፈው ሞ ፋራህ ኢትዮጵያውያኑን ከሚቀናቀኑት አትሌቶች መካከል ቀዳሚው ነው።

ኃይማኖት ጥሩነህ

እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic