ኢትዮጵያዊው ኬሚስት ዶክተር ካህሳይ ወልደ ጊዮርጊስ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 18.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ኢትዮጵያዊው ኬሚስት ዶክተር ካህሳይ ወልደ ጊዮርጊስ

ለከፍተኛ ትምህርት በመጡበት በጀርመን ሲኖሩ 47 ዓመታት ተቆጥረዋል ። ጀርመን የመጡት ኬምስትሪ ለማጥናት የነፃ ትምሕርት እድል አግኝተው ነበር ። በዚሁ የትምህርት ዘርፍ በተለይም በኦርጋኒክ ኬምስትሪ እዚሁ ጀርመን የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል ። ዶክተር ካህሳይ ወልደ ጊዮርጊስ ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:23

ዶክተር ካህሳይ ወልደ ጊዮርጊስ

ለከፍተኛ ትምህርት በመጡበት በጀርመን ሲኖሩ 47 ዓመታት ተቆጥረዋል ። ጀርመን የመጡት ኬምስትሪ ለማጥናት የነፃ ትምሕርት እድል አግኝተው ነበር ። በዚሁ የትምህርት ዘርፍ በተለይም በኦርጋኒክ ኬምስትሪ እዚሁ ጀርመን የዶክትሬት ዲግሪ አግኝተዋል ። ተወልደው ያደጉት የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት አዲስ አበባ ነው ። ጀርመን

መጥቶ የመማር እድል ያገኙትም ትምህርታቸውን በአዲስ አበባው የጀርመን ትምሕርት ቤት በማጠናቀቃቸው ነው ። ያኔ ከትምሕርት ቤቱ ነፃ የትምሕርት እድል አግኝተው ወደ ጀርመን ከመጡት ሁለት ኢትዮጵያውያን አንዱ ነበሩ ።ከአዲስ አበባው የጀርመን ትምሕርት ቤቱ የመጀመሪያው ምሩቃን አንዱ ዶክተር ካህሳይ በመረጡት ና በፈለጉት የትምህርት መስክ ነበር ጀርመን የመማር እድል ያገኙት ።ከምሁራን ቤተሰብ የወጡት ዶክተር ካሳዮ ጀርመን ከመሄዳቸው በፊት በጀርመን ትምህርት ቤት 10 ዓመት ጀርመንኛ በመማራቸው ህይወት በጀርመን አላስቸገራቸውም ።ከአንድ ህብረተሰብ ጋር ተዋህዶ ለመኖር ቋንቋ እጅግ ጠቃሚ መሣሪያ ነው ይላሉ ።

ዶክተር ካሳዮ በቱቢንገን ና በማይንዝ ዩኒቨርስቲዎች ኬሚስትሪ አጥንተው የማስትሬት ዲግሪ ቢያገኙም በዚህ ስላልረኩ በትምህርታቸው ገፍተው በዚሁ የትምህርት መስክ ለዶክትሪት ዲግሪያቸው ጥናታቸውን ቀጠሉ ። የመረረቂያ ጥንታቸው ትኩረትም ፕላስቲክ ነበር ።

የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላም ሲመኙ እንደነበረው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው ለተወሰኑ ዓመታት ሰርተዋል ።

ዶክተር ካህሳይ በውጭ ተፈላጊ በሆነ የእጣን ሰንደል ምርት ና ገበያ ውስጥም ይሰራሉ፤

ከሰለጠኑበት ከኬምስትሪ ሞያቸው በተጨማሪ ራሳቸውን በራሳቸው ባስተማሩት በኮምፕዩተር ትምህርት መስክም ጀርመን ውስጥ ለብዙ ዓመታት ሰርተዋል ። ወደ ዚህ ስራ የገቡበትን ሁኔታ ሲያስረዱ

ዶክተር ካህሳይ ጀርመን ውስጥ በበጎ አድራጎት ሥራም ውስጥ ይሳተፋሉ ለ25 ዓመታት አባል ሆነው የበኩላቸውን ድርሻ ያበረከቱበት ጀርመን ተምረው ወደ ሃገራቸው ለሚመለሱ የአፍሪቃን እስያውያን ተማሪዎች ምክርና ሥልጠና በሚሰጠው የጎቲንገኑ አፍሪካን ኤዥያን ስተዲስ ፕሮሞሽን በተባለው ድርጅት እንዲሁም በኋላ በተመሰረተው ፎረም ፎር ሰስቴይነብል ዴቨሎፕመነት ፎርአፍሪቃ ኤንድ ኤዥያ በተባለው ተመሳሳይ ድርጅት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል ። እዚሁ ዶክተር ካህሳይ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት እንዲሁም የሁለት ልጆች አያትም ናቸው ። በልጄ አስተዳደግ ውስጥ አንድ የሚቆጨኝ ነገር አለ ይላሉ ።

ጀርመን ለ47 ዓመታት የኖሩት ዶክተር ካህሳይ በ1990ዎቹ መጀመሪያ የዘረኞች ጥቃት ሰለባ ከመሆን ተርፈዋል። ይህንኑ ላይፕሲሽ ውስጥ ከዘረኞች ሊሰነዘርባቸው የነበረውን ጥቃት ምንጊዜም አይረሱትም ።

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic