ኢትዮጵያዊቷ ዐይነ ሥውር የሕግ ባለሙያ ተሸለሙ | ኢትዮጵያ | DW | 02.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዊቷ ዐይነ ሥውር የሕግ ባለሙያ ተሸለሙ

ኢትዮጵያዊቷ ዐይነ ሥውር የሕግ ባለሙያ የትነበርሽ ንጉሤን ጨምሮ  ሦስት የመብት ተሟጋቾች ትናንት ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ የ(Right Livelihood Award) የተሰኘው አማራጭ የኖቤል ሽልማት ተሰጣቸው።

ከ35 ዓመቷ ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሤ ጋር ትናንት በተከናወነው ስነ-ሥርአት የኖቤል ሽልማቱ የተሰጣቸው የአዘርባጃኗ ዘጋቢ ከድጃ ኢስማይሎቫ፤ የህንዱ ጠበቃ ኮሊን ጎንዛልቬስ ናቸው። በሽልማት ስነ-ሥርዓቱ ላይ የአዘርባጃኗ ዘጋቢ በጉዞ እገዳ ምክንያት መገኘት ባትችልም ስነ-ሥነስርዓቱን በቀጥታ በቪዲዮ መከታተሏ ተዘግቧል። ሽልማቱ በሕይወት ዘመናቸው ለሰብአዊ መብቶች መከበር፤ ለማኅበረሰብ ጤና እና መልካም አስተዳደር ተግዳሮቶችን ተጋፍጠው አንዳች ለውጥ ላመጡ ሰዎች የሚሰጥ ነው። በዘንድሮ አማራጭ የኖቤል ሽልማት 374,000 ዶላሩን ሽልማት ኢትዮጵያዊቷ የትነበርሽ ንጉሤ ከአዘርባጃኗ ዘጋቢ ከድጃ ኢስማይሎቫ እና ከህንዱ ጠበቃ ኮሊን ጎንዛልቬስ እንደሚካፈሉ የሽልማት ሰጪው ተቋም በድረ-ገጹ አትቷል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ልደት አበበ