ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት ተሸለሙ | አፍሪቃ | DW | 20.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ኢትዮጵያዊቷ ሳይንቲስት ተሸለሙ

ሎሪያል ተቋምና የተመ የትምህርት ሳይንስና ባህል ድርጅት ማለትም UNESCO በጋራ ያዘጋጁት 16ኛዉ የሳይንስ እና ሴቶች ልማት መርሃግብር ኢትዮጵያዊቷን ሳይንቲስት ዶክተር ሰገነት ቀለሙን ከዓመቱ ተሸላሚዎች አንዷ አድርጎ መረጠ።

ሁለቱም ተቋማት ሴቶች በሳይንሱ ዘርፍ በሚያደርጉት ምርምር ዕዉቅናን በመስጠት በማበረታታትና አጉልቶ በማዉጣት ከየአህጉሩ ለመረጧቸዉ አምስት እንስት ሳይንቲስት በየዓመቱ ሽልማት ይሰጣሉ፤ ለሎሬትነት ክብርም ያበቃሉ። ዘንድሮም በተለያዩ የምርምር ዘርፎች ልዩ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አምስት የዓለማችንን ምርጥ እንስት ሳይንቲስት የመረጡ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊቱ ዶክተር ሰገነት አፍሪቃና ከአረቡን ዓለም በመወከል ዛሬ ምሽት ላይ በሚከናወነዉ ሥርዓት ላይ ተሸላሚ ይሆናሉ። ዶክተሯ ተሸላሚ የሆኑት በእዕፅዋት ምርምር ዘርፍ ባካሄዱት ጥናት ምርጥ የሳር ዝርያን በማግኘታቸዉ እንደሆነ ታዉቋል።

የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተሸላሚዋን ሳይንቲስት አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ ልካልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነት

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic