ኢትዮጵያዉያን ዋናተኞች በኦሊምፒክ | ስፖርት | DW | 01.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

ኢትዮጵያዉያን ዋናተኞች በኦሊምፒክ

በኦሎምፒክ ታሪክ ኢትዮጵያ የምትታወቀዉ በሩጫ ዉድድር ተካፍለዉ ድልን በመጎናፀፍ የወርቅ እና ብር ሜዳሊያዎችን ተሸክመዉ በሚመለሱት ድንቅ አትሌቶቿ ነዉ። የዘንድሮዉ 30ኛዉ የሎንዶኑ ኦሎምፒክ ግን ለየት ባለ የስፖርት ዘርፍ የተሰለፉ

 ኢትዮጵያዉያንን ይዟል። ዋናተኞች። ለመጀመሪያ ጊዜ በሎንዶን ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ሁለት ዋናተኞችን አቅርባለች። ሆኖም ኢትዮጵያዉያኑ የዉሃ ዋና ተወዳዳሪዎች ካለ አሰልጣኝ ወደሎንዶኑ ኦሊምፒክ መምጣታቸዉ ነዉ የተሰማዉ። በዋና የሚወዳደሩት በሴቶች ያኔት ስዩም በወንዶች ደግሞ ሙሉዓለም ግርማን የሎንዶኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic