ኢትዮጵያዉያን በሊቢያ | ኢትዮጵያ | DW | 02.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያዉያን በሊቢያ

የኢትዮጵያ ቅጥረኛ ወታደሮች ወደ ሊቢያ ዘምተዋል የሚለዉን ዘገባም አምባሳደሩ አስተባብለዋል

default

የሌላ ሐገር ዜጎች በተገኘዉ መንገድ እየወጡ ነዉ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን ለመርዳት እየጣረ መሆኑን አስታወቀ። የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን አገዛዝ በመቃወም በተቀሰቀሰዉ ሕዝባዊ አመፅ ሰበብ ሊቢያ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካካል አንዳዶቹ መገደላቸዉ፥ሌሎቹ መደብደባቸዉን፥ ብዙዎች ደግሞ ምግብና መጠለያ ማጣታቸዉን ይናገራሉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ችግረኞቹን ለመርዳት ከሌሎች መንግሥታትና ከርዳታ ድርጅቶች ጋር እየሠራ ነዉ።የኢትዮጵያ ቅጥረኛ ወታደሮች ወደ ሊቢያ ዘምተዋል የሚለዉን ዘገባም አምባሳደሩ አስተባብለዋል።ነጋሽ መሐመድ አምባሳደር ዲናን በስልክ አነጋግሮቸዋል።

ሒሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

DW.COM