ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን | ዓለም | DW | 27.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን

ኢትዮጵያዉያን ጨምሮ 220 አፍሪቃዉያን ስደተኞችን ትናንት ወደ የሃገራቸዉ መመለስዋን የየመን ባለስልጣናት ገለፁ። የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት ዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ ባወጣዉ ዘገባ መሰረት የመን ወደየሃገራቸዉ ከመለሰቻቸዉ ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ በደቡባዊ የኤደን ወደብ ከተማ የነበሩ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ናቸዉ።  

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በየመን

 

 

የየመን ባለስልጣናት በገለፁት መሰረት ባለፉት ሁለት ሳምንታት 220 ስደተኞች ከመጡበት ከሶማልያ በኩል የተመለሱት በኤደን ባህር በኩል በመርከብ ተጭነዉ ነዉ። በየመን ሰንዓ የሚገኘዉ ተባባሪ ወኪላችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት ስደተኞቹ የተመለሱት ባለፈዉ ረቡዕና ቅዳሜ እለት ነዉ፤ የሚመለሱትም በዉዴታ ነዉ ሲል ገልጾአል።  በ

የመን

የሚታየዉ ረሃብና ጦርነት ካለዉ ሁኔታ ጋር ተዳምሮም ሁኔታዉ አሳሳቢ መሆኑን ነዉ ግሩም ተናግሮአል። በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት «IOM» የኮሙኒኬሽንስ ጉዳይ ባለሞያ አቶ አለማየሁ ሠይፈስላሴ ሰሞኑን ከየመን የተመለሰ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ አለመኖሩን ነገር ግን፤ ከጅቡቲ ወደ ሰባ ኢትዮጵያዉያን መመለሳቸዉን ተናግረዋል።  

ወደ ሀገራቸዉ ለመመለስ የሚፈልጉ ከ 2000 በላይ ኢትዮጵያዊያን የመንዉስጥ እንዳሉ የተናገሩት አቶ አለማየሁ ሠይፈ ስላሴ መሥርያ ቤታቸዉ በቀጣይ እነዚህን ዜጎች ለመመለስ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።    

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic